ስላቬን ቢሊች የዌስትሀም ደጋፊዎችን ይቅርታ ጠየቁ

ዌስትሀም ትናንት ምሽት በሜዳው ያደረገው ጨዋታ በብራይተን የ 3-0 ሽንፈት ካገጠመው በኋላ የቡድኑ አሰልጣኝ ስላቬን ቢሊች ይቅርታ ጠይቀዋል።

አርብ ምሽት ላይ በተደረገው የሳምንቱ የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ አዲስ መጪው ብራይተን ወደ ለንደን አቅንቶ ዌስትሀምን በሰፋ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችሏል።

የክሪስ ሁተኑ ቡድን በፕሪምየርሊጉ ከ34 አመት በኋላ ያገኘው ከሜዳው ውጪ ድል ሲሆን ለባለሜዳዎቹ አንገት የሚያስደፋ ውጤት ሆኖ አልፏል።

በውጤቱ የተበሳጩት እና ጫና ውስጥ የገቡት ስላቬን ቢሊች ለሽንፈቱ ጣታቸውን በማንም ተጫዋች ላይ እንደማይጦቁሙ በመናገር ሙሉ ሀላፊነቱን እራሳቸው እንደሚወስዱ አሳውቀዋል።

“ጎሎቹ ተጽእኖ ፈጥረውብናል።በተለይ የመጀመሪያው ጎል በጊዜ በመቆጠሩ ጎድቶናል።ሁለተኛው በተወሰነ መልኩ ጨዋታውን የገደለ ነበር

“ትንሽ ሪስክ ወስደን ተጫውተናል ነገርግን እነሱ በቁጥር በዝተው በደንብ አድርገው ተከላክለዋል ።ለዚህም ሊደነቁ ይገባል።

“በውጤቱ ተከፍቻለው።በካሜራ ፊት ተጫዋቾቼን ለሽንፈቱ ተጠያቂ አላደርጋቸውም።የቻሉትን አድርገዋል፣ነገርግን ጥረቱ በቂ አልነበረም

“ደጋፊዎችን ይቅርታ ማለት እፈልጋለው።እንዲህ የሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።እነሱ ከዚህ በላይ ይገባቸዋል።” ሲሉ ተናግረዋል።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s