ባርሴሎና ለ2017-18 የውድድር ዘመን በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን 879 ሚ.ዩሮ በጀት አፀደቀ

​ባርሴሎና በ2016-17 ክበረወሰን የሆነ ከፍተኛ ገቢ ማስገባቱን ተከትሎ ለ2017-18 የውድድ ዘመን በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን 897 ሚሊዮን ዩሮ በጀት አፅድቋል።

የላ ሊጋው ታላቅ ክለብ ዛሬ (ቅዳሜ) ባደረገው አጠቃላይ ስብሰባ በ2016-17 የውድድር ዘመን 708 ሚ.ዩሮ ገቢ መሰብሰቡ የተገለፀ ሲሆን፣ የክለቡ አባላትም ለቀጣዩ ዓመት ለክለቡ አዲስ ክብረወሰን የሚሰብር በጀትንም በተሰበሰበ 391 የድጋፍ ድምፅ እንዲሁም በ49 የተቃውሞ ድምፅ ወደተግባር እንዲገባ ውሳኔ አሳልፈዋል።

በክለቡ ከፍተኛ በተባለው ትርፍ ባርሴሎና በኔይማር ዝውውር ከፒኤስጂ ያገኘው 222 ሚ.ዩሮ አልተካተተም። 

ባርሴሎና በአድን የስራ ዓመት ያስገባውን ገቢ ከ700 ሚ.ዩሮ በላይ ሲያልፍ ይህ የመጀመሪያው ጊዜ ሲሆን ከ2010 አንስቶ ያለው የክለቡ ተቀማጭ ትርፉም 175 ሚ.ዩሮ ደርሷል። 

ምንም እንኳ የካታሎናውያኑን የራስን እድል በራስ የመወሰን ጥያቄ ተከትሎ በስፔን የፖለቲካ አለመረጋጋት ሊኖር ቢችልም ባርሴሎና ግን በ2021 ገቢውን 1 ቢሊዮን ዩሮ ለማድረስ ዕቅድ አስቀምጧል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s