መላ ያለተበጀለት አሳሳቢው የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳይ

Image may contain: one or more people

በአዲስ አበባ ስቴዲየም በ12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ የደረሰው ከባድ የተባለ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር በርካቶችን ያሳዘነ ሆኖ አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍጻሜው ጨዋታ በፊት ለቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ላሳያቹት የስፖርታዊ ጨዋነት እና የስቴዲየሙ ድምቀት ሽልማት ይገባቸዋል በማለት ለክለቦቹ የደጋፊዎች ማህበር አመራሮች የዋንጫ ሽልማት ቢያበረከትም ከጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ መጠናቀቅ በኋላ ግን የሆነው ሌላ ነበር፡፡

ከውድድሩ ጅማሮ አንስቶ በተለያዩ የሚዲያ አውታራት ሲወራለት እና ሲነገርለት የሰነበተው የደጋፊው ያማረ ድጋፍ በፍጻሜው በጨዋታው መጀመሪያ አጋማሽ እስኪጠናቀቅ በመጠኑ ቢታይም መጀመሪያ አጋማሽ መጠናቅ በኋላ ግን በተለምዶ ካታንጋ እየተባለ በሚጠራው የስቴዲየም የመቀመጫ ስፍራ  የተነሳው የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጸብ በርካቶችን ለጉዳት የዳረገ ሆኗል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ እያደር የእግር ኳስ ደረጃዋ እያሽቆለቀለ በእግር ኳሱ እምብዛም ስማቸውን በማናውቃቸው በነፓፓና ኒው ጊኒ ጭምር በደረጃ ሰንጠረዡ እየተበለጠች  ሊጉም ሆነ በሀገራችን የሚደረጉ የእግር ኳስ ውድድሮች ከማራኪነታቸው ይልቅ አሰልቺነታቸው በስፋት በሚነሳበት ወቅት እንዲህ አይነቶቹ አሳዛኝ የስቴዲየም ላይ የደጋፊዎችን ጸብ መመልከት በእጅጉ አሳዛኝ ነገር ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የአቋም መፈተሻ ውድድር ቢሆንም   የሁለቱ የከተማው ታላለቅ ክለቦች በፍጻሜው መገናኘታቸው ከፍተኛ ትኩረትን እንዲያገኝ አድርጎት ላለፉት ቀናት  በሰፋት ስለ ፍጻሜው ቢነገርም  መጨረሻው ግን  በርካቶችን ያስከፋ እና ያሳዘነ ሆኗል፡፡ ቁጥራቸው በርከት ያሉ የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎችም በእለቱ ከስቴዲየም በተወረወሩ ወንበሮች እና ድንጋዮች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ሲደርስባቸው ኳሱን በሰላማዊ መንገድ ሊታደሙ የመጡ ሴት ደጋፊዎችም ጉዳት ደርሶባቸው ራሳቸውን ስተው ታይተዋል፡፡

Image may contain: 3 people, people standing and outdoor

ይህም ከባድ የተባለ የስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈት ከወዲሁ ከአስራ እምስት ቀናት በኃላ ለሚጀምረው የኢትዪጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ስጋትን ከወዲሁ ፈጥሯል፡፡16 ክለቦች በሚሳተፉበት ሊግም እንደ ዛሬው አይነት የስፖርታዊ  ጨዋነት ጉድፈቶች እንዳይሰተናገዱም እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ እና ክለቦች በእግር ኳስ ተከታታዩ ደጋፊ ዙሪያ ከፍተኛ የተባለ የቤት ስራ እንዳለባቸው አሳይቷል፡፡

በተለይም ደግሞ እንደ አርአያ ሊታዪ የሚገቡት የ2ቱ አንጋፋ ክለቦች ደጋፊዎች  የእርስ በእርስ ጉሽሚያ እና ጸብ ለሀገሪቱ እግር ኳስ ሳንካ እና ችግር ከመሆን ውጪ ምንም ሊያመጣው የሚችለው እግር ኳሳዊ ለውጥ ስለሌ የሁለቱ ክለቦች አስተዳደሮች እና የደጋፊ አመራሮች በስፋት በጉዳዩ ላይ መምከር እና ዳግም እንዲህ አይነት ችግሮች ሊነሱ የማይችሉባቸውን አጋጣሚዎች ለመፍጠር ከወዲሁ ጠንከር ያሉ ስራዎችን መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s