ሲቲ ካፕ/ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በከፍተኛ የስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈት ታጅቦ ተጠናቀቀ


ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን በስቴዲየሙ የተስተዋለው እጅግ ኋላ ቀር የተመልካቾች ተግባር የብዙሃኑን ልብ አሳዝኗል፡፡

በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን ባገኘው ውድድር በቅድሚያ የተካሄደው በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በጅማ አባጅፋር መካከል የተደረገው የደረጃ ጨዋታ ሲሆን ተጋባዡ ጅማ አባጅፋር በሳምሶን ቆልቻ ጎል ድል አድርጎ መውጣት ችሏል፡፡ 

ከፌዴሬሽኑ የሚሰጠውን የጨዋታው ኮከብነት ሽልማት የጅማ አባጅፋሩ ሔኖክ አዱኛ ተሸልሟል፡፡

ቀጥሎ የተካሄደው በአገሪቱ ትልቅ የድጋፍ አቅም ባላቸው ሁለቱ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና መሃል የተደረገው የፍፃሜ ፍልሚያ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዲስ ፈራሚው ኢብራሒም ፎፎና ብቸኛ ጎል አሸንፎ የውድድሩን ሻምፒዮንነት ለአምስተኛ ጊዜ አውጇል፡፡

የዚህ ጨዋታ ኮከብ ተብሎ የተመረጠው የመሃል ተከላካዩ ሳላዲን ባርጊቾ ሲሆን ሌላኛው የቅዱስ ጊዮርጊስ አማካይ አብዱልከሪም ኒኪማ በበኩሉ የአጠቃላይ ውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ተሰኝቷል፡፡

የውድድሩን ኮከብ አስቆጣሪነት የኢትዮጵያ ቡናው ሳሙኤል ሳኑሚ እና የጅማ አባጅፋሩ ሳምሶን ቆልቻ በእኩል 3 ጎሎች አሸንፈዋል፡፡

በዚህ ጨዋታ መሃል በሁለቱ ክለቦች ደጋፊዎች መካከል የተነሳው ፀብ ወደአላስፈላጊ ድንጋይና ቁሳቁስ ውርወራ በማምራት በሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ አስገድዷል ፡፡ 

ይህ የደጋፊ ፀብ ብዙ መልካም ጎኖች የነበሩትን የዘንድሮውን ውድድር የማታ ማታ ከማጠልሸት ባለፈ ካለበት ፈቅ ሊል ቀርቶ ወደኋላ እየተጎተተ ላለው እግር ኳሳችን ሌላኛው ነቀርሳ የሆነ ነበር፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s