በካፍ ቻምፕየንስ ሊግ የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ ለፍጻሜ የሚያበቃውን ውጤት አስመዘገበ

​የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ የአልጄሪያውን ዩ ኤስ ኤም አልጀርን በማሸነፍ ለካፍ ቻምፕየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ መድረስ ቻለ።

ሁለቱ ቡድኖች አልጄሪያ ላይ ያደረጉት የመጀመሪያው ጨዋታ ያለ ጎል በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ የትናንት ምሽቱ የመልሱ ጨዋታ በከፍተኛ ጉጉት ተጠብቋል።

የ 1992 የካፍ ቻምፕየንስ ሊግ አሸናፊ የነበረው ዋይዳድ ካዛብላንካ በሜዳው ላይ ያለውን የዘንድሮ የበላይነት ማስጠበቅ ችሏል።

ቡድኑ ዘንድሮ ያደረጋቸው የሜዳው ስድስት የቻምፕየንስ ሊግ ጨዋታዎች በአሸናፊነት በመወጣቱ ወደ ፍጻሜ እንዲያቀና ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጎለታል።

በኤልካርቲ ጎል ቀዳሚ የሆኑት ባለሜዳዎቹ ከእረፍት መልስ ቤንቻርኪ ባስቆጠረው ጎል 2-0 መምራት ቢችሉም ተከላካዩ አሚር ቢቱቺ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ዋይዳዶችን ጫና ውስጥ ከቷቸው ታይቷል።

ይህን አጋጣሚም በመጠቀም  ዩ ኤስ ኤም አልጀርስ የመጀመሪያውን ጎል 68ኛው ደቂቃ ላይ በአዩብ  አብዲላዊ የመጀመሪያ ጎል ማስቆጠር ችለዋል።

ነገርግን ቤንቻርኪ በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃ ላይ ዋይዳዶችን ከጭንቀት የገላገለ ለራሱ ሁለተኛ ለቡድኑ ሶስተኛ ጎል በማስቆጠሩ ጨዋታው 3-1 ሊጠናቀቅ ችሏል።

ዋይዳድ በፍጻሜው የአል አህሊ እና የኢቶይል ዱ ሳህል አሸናፊ ጋር ለፍጻሜ የሚጫወት ይሆናል።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s