በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቲፒ ማዚምቤ ለፍጻሜ መድረሱን አረጋገጠ

የ 2015 የካፍ ቻምፕየንስ ሊግ እንዲሁም የ2016 የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሸናፊው ቲፒ ማዚምቤ ዘንድሮም በድጋሚ ለፍጻሜ ጨዋታ መድረስ የሚያስችለውን ውጤት አስመዝግቧል።

በአፍሪካ መድረክ በውጤታማነታቸው ከሚጠቀሱት ጥቂት ቡድኖች ውስጥ አንዱ የሆነው ቲፒ ማዚምቤ እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ለፍጻሜ መድረሱን አረጋግጧል።

2016 ላይ ለፍጻሜ ቀርቦ የነበረውን ሞ ቤጃያን 5-2 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት መሆን የቻለው ማዚምቤ ትናንት ምሽትም ወደ ሞሮኮ አቅንቶ ከፉስ ራባት ጋር በአቻ ውጤት በማጠናቀቁ ለፍጻሜ የሚያበቃውን ትኬት መቁረጥ ችለዋል።

ማዚምቤ በመጀመሪያው ጨዋታ በሜዳቸው 1-0 በማሸነፋቸው ራባት ላይ ያደረጉት የምሽቱ ጨዋታ 0-0 በመጠናቀቁ በአጠቃላይ ድምር አሸናፊ ሆነዋል።

በጨዋታው የመጀመሪያው ግማሽ በሁለቱም በኩል ጥቂት የጎል እድሎች የታዩበት ቢሆንም እንግዳው ቡድን ወደ ኋላ በማፈግፈግ በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት ሲሞክሩ ታይተዋል።

በሁለተኛው ግማሽ ተጭነው የተጫወቱት ፉስ ራባቶች በአጥቂው ብራሂም ኤል ባኸራኦይ አማካኝነት ያልተጠቀሙበት አጋጣሚ የሚያስቆጭ ነበር።

ሜስቻክ ኢሊያ ሬንፎርድ ካላባን ቀይሮ ከገባ በኋላ የፉስ ራባት ተከላካዮችን ሲያስጨንቅ ቢታይም በሁለቱም በኩል ጎል ሊቆጠር ባለመቻሉ ቲፒ ማዚምቤ ወደ ፍጻሜ አልፏል።

ለፍጻሜም ከሱፐር ስፓርት ዩናይትድ እና ከክለብ አፍሪካ አሸናፊ ጋር በህዳር ወር የሚጫወት ይሆናል።

ማዚምቤ የዋንጫ አሸናፉ ከሆነ ከ 2015 እስከ 2017 በተከታታይ አንድ የካፍ ቻምፕየንስ ሊግ እና ሁለት የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ በማንሳት በአፍሪካ ደማቅ ታሪክ መጻፉን ይቀጥላል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s