የቀድሞ የኤሲሚላን ተጫዋች ካካ ካላዜ የጆርጂያ ዋና ከተማ ትቢሊሲ ከንቲባ ሆኖ ተሾመ

እግርኳስ ካቆመ በኋላ ወደ ፓለቲካው የገባው የቀድሞ የኤሲ ሚላን ተጫዋች የነበረው ካካ ካላዜ የጆርጂያ ዋና ከተማ ቲቢሊሲ ከንቲባ ሆኖ ተመረጠ።

ለዋና ከተማው ከንቲባ ምርጫ ቅዳሜ በተሰበሰበ ድምጽ የ39 አመቱ ካካ ካላዜ 51% ድምጽ በማግኘት አሸናፊ መሆን ችሏል።

ካላዜ በሚላን ዘጠኝ አመት መቆየት ሲችል በቆይታው ሁለት የቻምፕየንስ ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ወደ ፓለቲካው ጊዜ ለመስጠት 2012 ላይ ጡረታ መውጣት ችሏል።

የቀድሞ የጆርጂያ ብሄራዊ ቡድን አምበል የነበረው ካላዜ ባለፈው አመት ፕሬዝዳንት ለመሆን ተወዳድሮ የነበረ ሲሆን በምርጫው የ”ኢቫንሹቪሊ ጥምረት” አሸናፊ በመሆኑ ካላዜ የ”ሀይል ሚኒስቴር” ሆኖ ቆይቷል።

ነገርግን ባለፈው ነሀሴ ወር ላይ ከሀላፊነቱ ለቆ የዋና ከተማዋ ቲቢሊሲ ከንቲባ ለመሆን ሲሰራ ከቆየ በኋላ በምርጫው አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።

.

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s