የ12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቁጥራዊ መረጃዎች

Image may contain: 2 people, people standing and outdoorላለፉት 2 ሳምንታት በአዲስ አበባ ስቴዲየም ሲካሄድ የሰነበተው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ዛሬ ምሽት በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ተጠናቋል ፡፡ የውድድሩ አበይት ቁጥራዊ መረጃዎችን ደግሞ ከታች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

ጅማሬው ውብ ሆኖ ፍጻሜው በስፖርታዊ ጨዋነት ጉድልት ያላማረው ይህ የከተማው ውድድር በርካታ አዳዲስ ጽንሰ ሀሳቦችን በመያዝ ለኢትዪጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጭምር አስተማሪ ሆኖ ያለፈ ሲሆን ከዛሬ አመሻሹ የደጋፊዎች ስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት ውጪ መልካም ነገሮችን አሳይቷል፡፡

በተለይም በህዝብ ግንኙነት ረገድ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሚዲያው ጋር የነበረው ቅርርብ እና የመረጃ አሰጣጥ ሂደት በእጅጉ መልካም የነበረ  እና ለሌሎችም ፌዴሬሽኖች ምሳሌ መሆን የሚችል ሲሆን ለዚህም የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በመሆን እየሰራ የሚገኘው ጋዜጠኛ ዮናስ ሀጎስ  ከፍተኛውን ሚና ይወስዳል፡፡

ለ9 ቀናጾች በተካሄደው በዚህ ውድድር 16 ጨዋታዎች በ8 ክለቦች መካከል የተደረጉ ሲሆን 21 ግቦች በ16ቱ ጨዋታዎች ከመረብ አርፈዋል፡፡ 48 ቢጫ ካርዶች በሁሉም ጨዋታዎች በዳኞች የተመዘዙ ሲሆን 1 ቀይ ካርድ ብቻ ተመልክቷል፡፡ አጠቃላይ እስካሁን ውድድሩን 167.275 ሰዎች በአዲስ አበባ ስቴዲየም በመታደም የተከታተሉ ሲሆን ይህም በአማካይ ሲሰላ የተገኘውን ተመልካች ቁጥር በ1 ጨዋታ 18.583 ያደርሰዋል፡፡

በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ ቡና በ5 ጨዋታዎች 5 ግቦችን በማስቆጠር በርካታ ግቦች ያስቆጠረ ክለብ ሲሆን ደደቢት እና መከላከያ በ3 ጨዋታዎች 1 ግብ ብቻ ማስቆጠራቸውን ተከትሎ የውድድሩን ዝቅተኛ ግብ ከመረብ ያገናኙ ክለቦች መሆን ችለዋል፡፡ ሌሎች የውድድሩ አበይት ቁጥራዊ መረጃዎችን ደግሞ ከታች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

  • ቅዱስ ጊዮርጊስ የውድድሩን ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡናን 1-0 በማሸነፍ ማንሳት የቻለ ሲሆን ይህም በውድድሩ ታሪክ 5ኛው ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡
  • የ12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ 3 የፍጹም ቅጣት ምት ግቦችን በ1 ጨዋታ ማስቆር የቻለው የኢትዮጵያ ቡናው ሳሙኤል ሳኑሚ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አግቢነት ክብርን በ3 ግቦች ከጅማ አባ ጅፋሩ ሳምሶን ቆልቻ ጋር በመሆን ማሸነፍ ችሏል፡፡ በዚህም 2ቱ ተጫዋቾች ከፌዴሬሽኑ የ10 ሺ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
  • በውድድር መልካም ብቃቱን ማሳየት የቻለው የቅዱስ ጊዮርጊሱ አማካይ ስፍራ ተጫዋች ቡርኪናፋሶዋዊ አብዱልከሪም ዞኮ ደግሞ የ12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ኮከብ ተጨዋች በመባል 20 ሺ ብር እና የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡
  • ቅዱስ ጊዮርጊስን የውድድሩ አሸናፊ እንዲሆን ያስቻሉት ፖርቱጋላዊው አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ የውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝ የተባሉ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ዋንጫ እና 22 ሺ ብር በሽልማት ሰጥቷቸዋል፡፡
  • የውድድሩን ሽልማቶች በብዛት የወሰደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በስፖርታዊ ጨዋነት የዋንጫ ተሸላሚ የሆነ ሲሆን ለዚህም በጨዋታዎች ላይ የተመለከቷቸው ካርዶች ዝቅተኛ መሆን ለአሸናፊነታቸው ግንባር ቀደሙን ሚና ተወጥቷል፡፡

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s