ሜሱት ኦዚል ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ይሄዳል በሚለው ዙሪያ ምላሹን ሰጠ

የአርሰናሉ የአጥቂ አማካይ የሆነው ሜሱት ኦዚል ወደ ማንችስተር ዩናይትድ እንደሚያቀና በሰፊው መወራቱን ተከትሎ ምላሹን ሰጥቷል።

አርሰናል ኤቨርተንን 5-2 ባሸበፈበት የእሁዱ የምሳ ሰአት ጨዋታ ላይ አንድ ጎል ማስቆጠር የቻለው ሜሱት ኦዚል በአመቱ መጨረሻ ላይ ከአርሰናል ጋር ያለው ኮንትራት ይጠናቀቃል።

እስካሁን ድረስ በክለቡ ስለመቆየቱ ያልታወቀው ጀርመናዊው አማካይን ለማስፈረም የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች በአይነ ቁራኛ እየተከታተሉት ይገኛል።

ወደ ቱርክ፣ጣሊያን ያቀናል የሚሉ መረጃዎች ሲወጡ የቆዩ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ ከቀድሞው አለቃው ጆሴ ሞሪንሆ ጋር በድጋሚ ሊገናኝ እንደሚችል በሰፊው ሲነገር ቆይቷል።

በተለይም የእንግሊዙ ሚረር ጋዜጣ በአርብ እትሙ የጀርባ ገጹ ላይ ተጫዋቹ ለማንችስተር ዩናይትድ እንደሚፈርም ይህንንም ለቡድን ጓደኞቹ መናገሩን ጨምሮ ይዞ ወጥቷል።

መረጃው ብዙዎቹን ሲያነጋግር የነበረ ሲሆን “ትጋቱ ቀንሷል” በማለት አንዳንድ የአርሰናል ደጋፊዎች ተጫዋቹ ከክለቡ ቢወጣ ጉዳት እንደሌላው ሲገልጹ፣ዩናይትዶች ደግሞ ተጫዋቹ ወደ ቡድናቸው ቢመጣ በየትኛው ቦታ ላይ ለመሰለፍ እድል ሊያገኝ እንደሚችል ሲያብሰለስሉ ቆይተዋል።

ነገርግን ተጫዋቹ በትዊተር ገጹ ብዙም ግልጽ ያልሆነ “ጩኸቱን ትታችሁ ትኩረታችሁን እንደያዛችሁ ቆዩ” የሚል መልእክት አስተላልፏል።

መልእክቱ ግልጽ ባለመሆኑ በብዙ መንገድ ሊተሮገም የሚችል ሲሆን አሁንም ተጫዋቹ ከጊዜው ለማረጋጋት እንጂ በጥር የዝውውር መስኮት ክለቡን ላለመልቀቁ የሚያሳይ መልእክት አልተናገረም የሚሉ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ ስለኔ የሚወራውን አትስሙ የሚል መልእት አለው በማለት ከክለቡ ጋር ለመቆየት አስቧል ብለው ትርጓሜ ሰጥተውታል።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s