ቶማስ ሙለር በገጠመው የቋንጃ ጉዳት ለሶስት ሳምንት ከሜዳ ይርቃል

ቶማስ ሙለር ባየር ሙኒክ ቅደሜ ከሀምቡርግ ጋር ባደረገው የቡንደስሊጋ ጨዋታ ላይ በገጠመው የቋንጃ ጉዳት ለሶስት ሳምንታት ከሜዳ ርቆ እንደሚቆይ ክለቡ ገልፅዋል።

የጀርመናዊ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቹ ባየር ሙኒክ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፈ በቻለበት ጨዋታ በወቅቱ በጉዳት ምክኒያት ጨዋታውን ለቆ ለመውጣት ከመገደዱ በፊት በጨዋታው ላይ መቆየት የቻለው ለ10 ደቂቃዎች ያህል ብቻ ነበር።

እሁድ ዕለት ከተደረገለት የህክምና ምርመራ በኋላ ባየር ሙኒክ ተጫዋቹ እስከሚቀጥለው ወር አጋማሽ ድረስ ወደሜዳ እንደማይመለስ በመግለፅ ሙሉ የጉዳቱን ሁኔታ ይፋ አድርጓል።

የሙለር ጉዳት አሰልጣኙ የፕ ሄይንክስ አርብ ዕለት ወደቀድሞ ድንቅ ብቃቱ ለመመለስ መቃረቡን ከገለፁ በኋላ የተከሰተም መሆኑ ሁኔታውን መጥፎ ዕድል አድርጎበታል።

ሙለር ይህን ጉዳቱን ተከትሎም ከአርቢ ሌፕዚግ ጋር በቀጣዮቹ አምስት ቀናት የሚደረጉትን የጀርመን ዋንጫ እና የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች ጨምሮ በርካታ ወሳኝ ጨዋታዎች የሚያመልጡትም ይሆናል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s