የተረጋገጠ / ኤቨርተን ሮናልድ ኩማንን ማሰናበቱ አሳወቀ

የመርሲሳይዱ ኤቨርተን ሆላንዳዊውን የቡድኑን አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማንን ማሰናበቱ ይፋ አደረገ።

የ2017/2018 የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ከተጀመረ በኋላ ደካማ አጀማመር ያደረገው ኤቨርተን ከመጨረሻ በሶስተኛ ላይ ተቀምጧል።

ትናንት በሜዳው ያደረገው ጨዋታም በአርሰናል በሰፋ ጎል የተሸነፈ ሲሆን የአሰልጣኙ ሮናልድ ኩማን ቆይታም የመጨረሻው ሆኗል።

የትናንቱ የቡድኑ ሽንፈት በሁሉም ውድድሮች ካደረጋቸው 11 ጨዋታዎች ውስጥ ሰባተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

በሰኔ 2016 ላይ በአመት 6 ሚሊየን ፓውንድ እየተከፈላቸው የመርሲሳይዱን ቡድን ለማሰልጠን የተስማሙት ኩማን ኤቨርተን ሰባተኛ ሆኖ እንዲያጠናቅቅ ማድረግ ችለው ነበር።

ነገርግን 140 ሚሊየን ፓውንድ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ ወጪ ካደረጉ በኋላ ቡድኑ ሌሎቹ ታላለቅ ቡድኖችን መፎካከር እንደሚችል ተጠብቆ ነበር።

በክረምቱ የተዛወሩት ተጫዋቾች እንደተጠበቁት ያለመሆን ወይንም ተጽእኗቸው አነስተኛ ሆኖ መታየቱ ቡድኑ ላይ ለውጥ ለመፍጠር ባለመቻላቸው ለቡድኑ ድክመት ተጠቃሽ ሆኗል።

ኤቨርተን ለጊዜው የቡድኑ ከ 23 አመት በታች አሰልጣኝ ዋና ቡድኑን እንደሚመሩት ታውቋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s