ግብጽ የ2018 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፕዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ እንደማትሳተፍ አሳወቀች 

ካፍ ኬኒያን ተክታ ግብጽ በ 2018 የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ብቻ በሚሳተፉበት የአፍሪካ ሀገራት ሻምፕዮንሺፕ(ቻን) ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ ቢያሳውቅም የግብጽ እግርኳስ ማህበር በውድድሩ ላይ ላለመሳተፍ መወሰኑ ታውቋል።

በዝግጅት ማነስ ምክኒያት ከሳምንት በፊት ከኬኒያ ተነስቶ ለሞሮኮ የተሰጠው የ2018 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፕዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ከወር በኋላ ይጀመራል።

ሞሮኮ የአዘጋጅነት እድል በቅርቡ በማግኘቷ በውድድሩ ላይ በቀጥታ ተሳታፊ የምትሆን ሲሆን አዘጋጅ ባትሆንም ቀደም ብላ የሰሜኑን ዞን ግብጽን በማሸነፏ በውድድሩ ላይ መሳተፏ የማይቀር ነበር።

አሁን ግን አዘጋጅ በመሆኗ ኬኒያን ተክታ በሞሮኮ የተሸነፈችው ግብጽ በውድድሩ ላይ እንድትሳተፍ ካፍ ማሳወቁ ይታወቃል።

ነገርግን የግብጽ እግርኳስ ማህበር በውድድሩ ላይ ከመሳተፍ ይልቅ የሀገሬን ፕሪምየርሊግ ማካሄድ ይሻለኛል በማለት የተሳትፎውን ጥሪ እንደማትቀበለው ታውቋል።

“ለካፍ በውድድሩ ላይ እንደማንሳተፍ ደብዳቤ ጽፈናል።ምክንያታችን ደግሞ ውድድሩ በፊፋ መርሀግብር ውስጥ ስለማይካተት የውስጥ የፕሪምየርሊግ ውድድሮችን ማቋረጥ አንችልም።” በማለት የእግርኳስ ማህበሩ ዳይሬክተር የሆኑት ታርዋት ስዊላም አሳውቀዋል።

ካፍ የግብጽ ጥያቄ ላይ የሚሰጠው ምላሽ ይጠበቃል።


Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s