ሪያን ጊግስ ለማንችስተር ዩናይትዱ ቪክቶር ሊንድሎፍ ድጋፉን ሰጠ

ማንችስተር ዩናይትድ በሀደርስፊልድ በተሸነፈበት ጨዋታ ለሁለተኛዋ ጎል መቆጠር ምክንያት የሆነውና ጠንካራ ትችት በደጋፊዎች ለቀረበበት ለቪክቶር ሊንድሎፍ ሪያን ጊግስ ድጋፉን ሰጥቷል።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት 31 ሚሊየን ፓውንድ ወጥቶበት ከቤኒፊካ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የተዘዋወረው ቪክቶር ሊንድሎፍ ከቡድኑ ጋር ቶሎ መላመድ አልቻለም።

በጆሴ ሞሪንሆ ቡድን ውስጥ በቋሚነት መሰለፍ እድል ማግኘት ያልቻለ ሲሆን አልፎ አልፎ ተቀይሮ ሲገባም ማራኪ እንቅስቃሴ ማድረግ ተስኖታል።

ተጫዋቹ ባሳለፍነው ቅዳሜ የፊል ጆንስን መጎዳት ተከትሎ ተቀይሮ ወደ ሜዳ ቢገባም ቡድኑን ዋጋ ያስከፈለ ስህተት መስራት ችሏል።

የሰራው ስህተት ለሁለተኛዋ ጎል መቆጠር ምክንያት የሆነ ሲሆን ቡድኑ በመሸነፉ ከደጋፊዎች ጠንካራ ትችት ቀርቦበታል።

ነገርግን የቀድሞ የቡድኑ ተጫዋች የሆነው ሪያን ጊግስ ተጫዋቹ እንደ ስታም፣ቪዲች እና ኤቭራ ጥሩ ይሆናል በማለት ድጋፉን ሰጥቶታል።”

​”በአሁን ሰአት ብዙ ትችት እየቀረበበት ያለው ቪክቶር ሊንድሎፍ ነው።ነገርግን በእርግጠኝነት ከጨዋታው ውጪ ልናደርገው አንችልም።አንዳንድ ተጫዋቾች በፕሪምየርሊጉ ቶሎ ሲለምዱ ሌሎች ደግሞ ስድስት ወር ወይንም አንድ አመት ሊፈጅባቸው ይችላል።

“ስታሸንፍም ይሁን ስትሸነፍ በአንድ ላይ ነው እንጂ አንድ ተጫዋችን ለይተህ አታወጣም።ለዚያውም በቋሚነት ላልተጫወተ ተጫዋች።ሊንድሎፍም ይህንንም ተቋቁሞ በጥሩ መንገድ እንደሚጓዝ አስባለው።”ሲል ተናግሯል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s