ሮናልዶ ለተከታታይ ሁለት ዓመታት የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት አሸናፊ ሆነ

ሪያል ማድሪድን ለተከታታይ ሁለት ዓመታት የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማንሳት እንዲችል ማድረግ የቻለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለተከታታይ ሁለት ዓመታት የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ወንድ ተጫዋች ሽልማትን ማግኘት ችሏል።

ፖርቱጋላዊው ኮከብ ቀንኛ ተቀናቃኙን ሊዮኔል መሲንና የአርጄንቲናዊውን የቀድሞ የባርሴሎና አጋር ብራዚላዊውን ኔይማርን በምርጫው በመቅደም የሽልማቱ አሸናፊ ሆኗል።

ሮናልዶ የምርጥ ተጫዋችነት ሽልማቱን ለመቀዳጅ ባለፈው የውድድር ዘመን ለሪያል ማድሪድ ስኬት ያበረከተው አስተዋፅኦ ወሳኝ ሚና የነበረው ሲሆን፣ የ32 ዓመቱ ተጫዋች በሁሉም ውድድሮች ላይ 42 ግቦች ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሎ ነበር።

ሮናልዶ በላ ሊጋው ያስቆጠራቸው 25 ግቦች በሊጉ ከመሲና ልዊስ ስዋሬዝ ቀጥሎ በኮከብ ተጫዋችነት በሶስተኝነት ደረጀ መቀመጥ ሲያስችለው፣ በ13 የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ ደግሞ በፍፃሜው ጨዋታ በጁቬንቱስ ላይ ያስቆጠራቸውን ሁለት ግቦች ጨምሮ 12 ግቦችንም ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል።

ሮናልዶ በለንደኑ ፓላዲየም ሽልማቱን ከተቀበለ በኋለ ባደረገው ንግግር ምሽቱን ከጎኑ በመቀመጥ አብረውት ላሳለፉ መሲን እና ኔይማር ያለውን አድናቆት ገልፅዋል።

“የመረጡኝን ሁሉ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ።  ሊዮ እና መሲ እዚህ በመገኘታቸውም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።” ሲል ተናግሮ። አክሎም “ሪያል ማድሪድ አሰልጣኙ፣ ደጋፊው፣ ፕሬዝዳንቱ ዓመቱን በሙሉ ድጋፍ ሲሰጡኝ ነበር። ስለዚህ አመሰግናችኋለሁ እላለሁ።

“ለተከታታይ ጊዜ ሽልማቱን በማግኘቴም በእጅጉ ደስታ ይስማኛል። ይህ ጊዜ ለእኔ ታላቅ ነው። በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ደጋፊዎች በሙሉ ለሰጣችሁኝ ድጋፍ አመሰግናለሁ። ለዚያም ትልቅ አድናቆት አለኝ። በጣም አመሰግናለሁ።

“በእዚህ ከታላላቅ ተጫዋቾች ጋር መገኘት ትልቅ ነገር ነው። እናም ሰዎች በእዚህ ደስተኛ ነኝ። በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ።” ብሏል።

መሲ ምንም እንኳ ግላዊ ስኬቱ ከግምት ውስጥ ባይገባለትም በግሉ ባደረጋቸው 52 ጨዋታዎች በ54 ግቦችን እና 16 የግብ እድሎችን በመፈጥረ አስደናቂ የውድድር ዘመን ማሰለፍ ችሎ ነበር።

ይህ ዓመትም ለመሲ በተካታታይ ሁለት ዓመታት ከሮናልዶ ቀጥሎ በሁለተኝነት ምርጥ ተጫዋች የተሰኘበት ዓመት ሆኗል።

በእዚህ ዓመት የዓለም የዝውውር ክብረወሰን በሆነ ዋጋ ፒኤስጂን የተቀላቀለው ኔይማር ባለፈው ሽልማት በሶስተኝነት ያጠናቀቀውን አንትዋን ግሪዝማንን ተክቶ ሽልማቱን ተቀብሏል።

ዚነዲን ዚዳን የፊፋ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝነት ሽልማትን ሲቀዳጅ፣ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂነት ሽልማትን ደግሞ ጂያንሉጂ ቡፎን አሸንፏል። 

በሌሎች ሽልማቶች የአርሰናሉ አጥቂ ኦሊቪየ ዥሩ የፑሽካሽ (የዓመቱ ምርጥ ግብ) ተሸላሚ፣ ሆላንዳዊቷ ሳሪና ዊግማን የዓመቱ ምርጥ የሴቶች አሰልጣኝ ሽልማት አሸናፊ መሆን ችለዋል።
በዓመቱ ምርጥ ደጋፊዎች ሽልማት የሴልቲክ ደጋፊዎች፣ የፊፋ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት ፍራነሢስ ኮኔ፣ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ሴት ተጫዋች ሌኬ መርተንስ ሆነው ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

በፊፋ የዓመቱ ምርጥ ቡድን 11 ዝርዝር ውስጥ ደግሞ ቡፎን፣ አልቬስ፣ ራሞስ፣ ቦኑቺ፣ ማርሴሎ፣ ሞድሪች፣ ክሩዝ፣ ኢንየስታ፣ መሲ፣ ኔይማር እና ሮናልዶ ተካተዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s