በጣሊያን ከጨዋታ በፊት ከአና ፍራንክ ግለታሪክ መፃህፍ አንድ ገፅ እንዲነበብ ሊደረግ ነው

የጣሊያን እግርኳስ ማህበር ከዚህ ሳምንት አንስተው በሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎትና የጅምላ ዘር ማጥፋት ወንጀል ከተፈፀመባት አና ፍራንክ ግለ ታሪክ አንድ ገፅ እንዲነበብ የሚያስገድድ ትዕዛዝ አስታልፏል። 

ትዕዛዙ በሃገሪቱ እየተስፋፋ የመጣውን የፀረ ሴማዊ ባህሪያት ተከትሎ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች በጣሊያን በሚደረጉ በሁሉም ፕሮፌሽናል፣ አማተር እና የወጣቶች ጨዋታዎች በፊት ለተወሰኑ ደቂቃዎች በዝምታ የህሊና ፀሎቱና ንባቡ እንዲደረግ ያስገድዳል።

አና ፍራንክ ትውልደ ጀርመናዊት ይሁዲ ስትሆን፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ግድያ የተፈፀመባት ታዳጊ ነበረች። ታዳጊዋ በፃፈችው ግለታሪክዋም በመላው ዓለም በከፍተዝኛ ሁኔታ የናኘ ስም ማትረፍ ችላለች።

ቅዳሜ በተደረገው ጨዋታ የላዚዮ ደጋፊዎች የአናን ምስል የቀንደኛ ተቀናቃኛቸውን መለያ አልብሰው እና ፀረ ሴማዊ መልዕክት የሚያስተላለፍ መልዕክት አንገበው በመላው ስታዲየም ታይተዋል።

በዚህ የዘረዝኝነት ጥፋታቸውም የላዚዮ ደጋፊዎች በጣሊያን እግርኳስ ማህበር ቅጣት ተላልፎበቸዋል።

ከአና ፍራንክ ግለ ታሪክ መካከል የሚነበበው ገፅ “ዓለም ቀስ በቀስ ወደጫካነት ስትለወጥ ተመለከትኩ። እንድ ቀን የሚያጠፋን የመብረቅ ነጎድጓድም ሰማሁ። የሚሊዮኖችም ስቃይ ተሰማኝ።

“ወደሰማይ አንጋጥጬ ስመለከትም ይህ ሁሉ ጭካኔ፣ እንደሚያበቃ፣ ዳግም ሰላምና መረጋጋት እንደሚመጣ ተስማኝ። ሁሉም ነገር ወደተሻለ ነገር እንደሚቀየርም ተረዳሁ።” የሚለው ሊሆን እንደሚችል ዘገባዎች አመልክተዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s