ቬንገር የ18 ዓመቱ ንኬታህ “ፍራቻ” እንደሌለበት ገለፁ

የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ወጣቱ የፊት ተጫዋች ኤዲ ንኬታህ በእንግሊዝ የሊግ ካፕ ጨዋታ ባሳየው የጀግንነት ባህሪ እና እንቅስቃሴ የተሰማቸውን አድናቆት ገልፅዋል።

የ18 ዓመቱ ንኬታህ ከተቀያሪ ወንበር በመነሳት አርሰናል ማክሰኞ ምሽት በኤመራትስ ኖርዊች ሲቲን 2ለ1 መርታት የቻለባቸውን ሁለት ግቦች ማስቆጠር ችሏል።

ቬንገር ስለተጫዋቹ ሲናገሩ ወጣቱ ተጫዋች ከተቀያሪ ወንበር ተነስቶ ጨዋታ የማደረግ አቅም ያለው ተጫዋች እንደሆነ ገልፀው “[የማሸነፍ] ባህሪያት እንዳሉትና ፍራቻ እንደሌለበት አውቃለሁ።” ሲሉ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል።

“የእንቅስቃሴ ቅንጅቶችን ይረዳል። ኳስ አቀብሎ መሄድን ያውቅበታል። እንደእሱ ዓይነት ተጫዋቾች አንድ ጊዜ ወደጨዋታው ሲገቡ ሁልጊዜም [የግብ] ዕድል አላቸው።” ሲሉም አክለው ገልፀዋል።

ቬንገር በርካታ ልምድ ያላችው አጥቂዎች በተቀያሪ ወንበር ላይ ቢኖሩ ኖሮ ንኬታህን ወደሜዳ ገብቶ እንዲጫወት ሊያደረጉት አይችሉ እንደነበርም አምነዋል።

ፈረንሳዊው አሰልጣኝ የተጫዋቹ ተቀይሮ መግባት በግለፅ አርሰናልን አደገኛ እንዳደረግው እና ኒኪታህ በ96ኛው ደቂቃ የአሸንፊነቱን ግብ ማስቆጠር እንደቻለም ተናገረዋል።

“የሃሳብ እጥረት ነበረብን። በተወሰነ መልኩ ቆርጦ በመግባት የግብ ዕድል የመፈጠረ ክፍተት ነበረብን።” ሲሉም ቬንገር ተገልፀዋል።

“በኖርዊች የመከላከል ብቃት ተደንቄያለሁ። እናም ያለህ አማራጭ በተቀያሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብለህ ‘ይበልጥ አደገኛ ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ?’ እያልክ ማሰብ ብቻ ነው። 

“ትልቅ ቁማር የምንጫወትበት አጋጣሚ ይህ ነበር። ምክኒያቱም ወደፊት የሚያራምድ በቂ ጊዜ አልነበረንም። ደግሞም ኤዲ ግብ ማስቆጠር እንደሚችል አውቃለሁ።” ሲሉ ቬንገር ተናግረዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s