የሀደርስፊልዱ ወጣቱ ደጋፊ አስገራሚ ተግባር!

5.jpg

አዲስ አዳጊው ሀደርስፊልድ በሳምንቱ መጨረሻ ማንቸስተር ዩናይትድን በማሸነፍ አስደናቂ ድል ካስመዘገበ በኋላ አንድ ደጋፊ ያደረገው ተግባር እስካሁን አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

ዩናይትዶች የአመቱን የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን በቀመሱበት ጨዋታ ላይ ባለሜዳዎቹ ክፍተት በማይሰጥ ጥብቅ የመከላከል እና ፈጣን የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ የበላይ ሆነው አጠናቀዋል፡፡

ሀደርስፊልዶች የመረጡት እንቅስቃሴ ዩናይትዶችን የመጫወቻ ቦታ በማሳጣት በታክቲኩ ረገድ የተሸሉ የነበሩ ሲሆን ከጨዋታው በኋላም በጆሴ ሞሪንሆ አድናቆትን አግኝተዋል፡፡

በእለቱ ጎሉን ካስቆጠሩት ውስጥ አውስታራሊያዊው አሮን ሙይ የሚጠቀስ ሲሆን የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር ቡድናቸው አሸናፊ እንዲሆን ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡

በእለቱ አሮን ብሀና የሚባለው ደጋፊ በስታድየሙ 5 ፓውንድ ወድቆ አግኝቶ የነበረ ሲሆን ብሩን ከደብዳቤ ጋር በማድረግ ምርጥ እንቅስቃሴ ላደረገው አሮን ሙይ እንዲደርስ  ለክለቡ ዳይሬክተር ሲን ጃርቪስ ልኳል፡፡

ልብ የሚነካው ደብዳቤ እንዲህ ይላል “እኔ በዩናይትዱ ጨዋታ ላይ ሀደርስፊልድ ነበርኩ፡፡በስታድየሙም 5 ፓውንድ በማግኘቴ ለአባቴ ሰጥቼዋለው፡፡ምክንያቱም የኔን ያልሆነ ነገር መያዝ ስለማልፈልግ ነበር፡፡በመቀጠልም ብሩንም በፓስታ አድርጌ በእለቱ ምርጥ እንቅስቃሴ ላደረገው አሮን ሙይ ልኬለታለው፡፡”የሚል ነበር፡፡

ፓስታው የደረሳቸው ክለቡ ዳይሬክተር ደብዳቤውን በማህበራዊ ድረገጾች ላይ በመልቀቅ መነጋገሪያ እንዲሆን አድርገውታል፡፡አውስትራላዊው አሮን ሙይም ወጣቱን ደጋፊ ለማግኘት ፍላጎት እንዳለው ተናግሯል፡፡

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s