የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን በአለም ከ17 አመት በታች ዋንጫ ፍጻሜ አለፈ

Image result for Brazil U17 1-3 England U17 recap

በህንድ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2017 የአለም ከ17 አመት በታች የአለም ዋንጫ ላይ ድንቅ ብቃታቸውን እያሳዩ የሚገኙት የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ታዳጊዎች ለውድድሩ ከፍተኛ ቅድመ ግምት አግኝታ የነበረችውን ብራዚልን 3-1 በመርታት ለቅዳሜ ምሽቱ የዋንጫ ጨዋታ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በስቲቭ ኮፐር የሚመሩት ታዳጊዎቹ እጅግ ሞቃታማ የሆነው የኮልኮላታ አየር ንብረት ሳይገድባቸው የብራዚል አቻቸውን በታዳጊው የሊቨርፑል ተስፈኛ ኮከብ  ሪሃን ብሪውስተር ሶስት ግቦች መርታት የቻሉ ሲሆን ከወዲሁም ማሊን በተመሳሳይ 3-1 በመርታት ለፍጻሜው መብቃቷን ያረጋጠቸውን የስፔን ብሄራዊ ቡድንን ለፍጻሜው የሚገጥሙ ይሆናል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ባሳለፍነው ክረምት በአውሮፓ ከ17 አመት በታች ታዳጊዎች የአለም ዋንጫ ፍጻሜ ላይ ተገናኘተው ስፔን በመለያ ምት ማሸነፏ  ይታወሳል፡፡

የእንግሊዝ ብሄራዊ ታዳጊ ቡድን በ2017 በኮሪያ ተዘጋጅቶ በነበረው የአለም ከ20 አመት በታች የአለም ዋንጫ ላይም ስኬታማ ጊዜን ማሳለፍ የቻለ ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜን የመድረኩን ዋንጫ ከፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s