የማንችስተር ሲቲው አማካይ ያያ ቱሬ በካራባኦ ካፕ ትናንት ምሽት ዎልቭስን ሲያሸንፉ የተጫወቱባት ኳስ ከጇቡላኒ የባሰች ሲል ተችቷል።
ሲቲዎች ትናንት ምሽት ያደረጉት ጨዋታ ጎል ማስቆጠር ባለመቻላቸው በመለያ ምት ማሸነፍ ችለዋል።
ነገርግን የተጫወቱበት ኳስ አሰልጣኙን ፔፕ ጓርዲዮላንና አንዳንድ ተጫዋቾችን ማስደሰት አልቻለም።
ጓርዲዮላ ኳሷን ቀላል እና “ተቀባይነት የሌላት” በማለት ትችቱን ሲያቀርብ ያያ ቱሬም በተመሳሳይ በኳሱ ምቾት እንዳልተሰማው ተናግሯል።
“እውነት ለመናገር ኳሱን አልወደድኩትም።ኳሷ በጣም ቀላል ነች።በሀገሬ እንኳን እንደዚህ አይነት ኳስ አይጠቀሙም።የማይረባ ኳስ ነው።አምራቾቹ አሁን ካለው የተሻለ መስራት እንደሚችሉ አስባለው።”ሲል ተናግሯል።
ቱሬ ኳሷ ስትመታ ስስ እንደሆነች፣ ከማቆምም ሲሞከር እንደምታሟልጭ እንዲሁም በነበረው የአየር ንብረት ለመጫወት አመቺ አለመሆኗን ጨምሮ ገልጿል።
Advertisements