ጂያንሊውጂ ቡፎን ከአለም ዋንጫው በኋላ ጓንቱን ለመስቀል አቅዷል

 

 

Champions League win is the only thing that could see Gianluigi Buffon extend his careerአለማችን ካፈራቻቸው ምርጥ ግብ ጠባቂዎች መካከል በቀዳሚነት ስሙ የሚነሳው የ39 አመቱ ጣሊያናዊው ጂያንሊውጂ ቡፎን ከአለም ዋንጫው መጠናቀቅ በኋላ ጓንቱን ሊሰቅል እንደሚችል ተናግሯል፡፡

አመለ ሸጋው ግብ ጠባቂ ባሳለፍነው ሰኞ ምሽት በለንደን በተካሄደው የአመቱ የፊፋ ኮከብ ተጫዋቾች ምርጫ ላይ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ክብርን ባገኘ ማግስት ከዚህ አመት በኋላ ጡረታ እንደሚወጣ  ተናግሯል፡፡

ከስካይ ኢታሊያ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ ያደረገው ኮከብም  “ይህ የመጨረሻ የውድድር አመቴ ነው ፡፡ ይህ ውሳኔም ትክክለኛው ነው ብዮ አስብላው ከዚህ በኋላ ለተጨማሪ 1 ወይም 2 አመት የመጫወት አቅም ቢኖርኝም በተጫዋችነት ዘመኔ የምፈልጋቸውን ድሎች አሳክቻለው ፡፡” ከውድድር አመቱ መጠናቀቅ በኋላ ስንብቱን እንደሚያውጅ አሳውቋል፡፡

ቡፎን በዚህ አመት ማሳካት ስለሚፈለግው እቅድ ሲናገርም  በዚህ አመት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ከክለቤ ጁቬንቱስ ጋር ማንሳት እፈልጋል በተጨማሪም ለ2018 የአለም ዋንጫ ሀገሬን ማሳለፍ እና በውድድሩ መካፈል ቀዳሚው እቅዴ ነው ሲል በዚህ አመት ሊከውናቸውን ተግባራት አሳውቋል፡

ጣሊያናዊው የግብ ዘብ ባለፉት አመታት የእግር ኳስ ህይወቱ 8 የሴሪያ 4 የኮፓ ኢታሊያ ዋንጫዎችን ከፍ ያደረገ ሲሆን ለ 3 ጊዜያት ያህልም በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ለፍጻሜ መድረስ ችሏል፡፡ በ2006 የአለም ዋንጫን ከፍ ያደረገው የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን አባልም ነበር፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s