በላሊጋው ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በቪድዮ የታገዘ ዳኝነት(VAR) እንደሚጀመር ታወቀ

የስፔን እግርኳስ ማህበር ከቀጣዩ አመት ጀምሮ በላሊጋው በቪድዮ የታገዘ ዳኝነት(VAR) እንደሚጀምር አሳወቀ።

የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሁዋን ልዊስ ላሪያ ከቀጣይ አመት ጀምሮ ላሊጋው እንደ ቡንደስሊጋው እና ሴሪ ኣው በቪድዮ የታገዘ ዳኝነት(VAR) ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

የስፔኑ ራዲዮ የሆነው ካዴና ሰር  ሁዋን ልዊስ ላሪያን መቼ ሊጀምሩ እንደሚችሉ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ፕሬዝዳንቱም “ፍላጎታችን በቀጣይ አመት ነው።አሁን ቴክኖሎጂ ወደ እግርኳስ መጥቷል ስለዚህ መቀበል አለብህ።”በማለት ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

ላሪያ ጨምረው ቴክኖሎጂው በመላው ስፔን ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ከ70 በላይ በሚሆኑ ጨዋታዎች ላይ ሙከራ ላይ እንደሚውል አሳውቀዋል።

አዲሱ ቴክኖሎጂ መተግበር ከጀመረ ጀምሮ በተለያዩ አገራት እየተስፋፋ የሚገኝ ሲሆን አሁንም በቴክኖሎጂው ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ የሚገኙ አልጠፉም።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s