የተረጋገጠ / ሌሲስተር ሲቲ ክላውድ ፑኤልን የቡድኑ አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን አሳወቀ

የቀድሞ የሳውዝሀምፕተን አሰልጣኝ የነበሩት ክላውድ ፑኤል ከአራት ወራት እረፍት በኋላ የሌሲስተር ሲቲ አሰልጣኝ ተደርገው ተሾሙ።

ክሬግ ሼክስፒርን ካሰናበተ በኋላ አሰልጣኝ ሲያፈላልጉ የቆዩት የ 2015/2016 የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ አሸናፊዎቹ ሌሲስተር ሲቲዎች ከሁለት የተሳኩ ቃለመጠይቆች ካደረጉ በኋላ ምርጫቸውን ክላውድ ፑኤል ላይ አድርገዋል።

ሌሲስተሮች እንደ ካርሎ አንቼሎቲ፣ቶማስ ቱኸል እና ማኑኤል ፔሌግሪኒ አይነት ስማቸው ከፍ ያለ አሰልጣኝ ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ቢጠበቅም ሳይታሰብ ፑኤል መቅጠራቸው አሳውቀዋል።

አሰልጣኙ በኪንግፓወር ስታድየም ለሁለት አመት ተኩል ለመቆየት ፊርማቸውን ሲያኖሩ በክለቡም እንደ 2015/2016 ጠንካራ ተፎካካሪ ቡድን የመገንባት ሀላፊነት ተረክበዋል።

ፑኤል ሳውዝሀምፕተንን ለሊግ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ በማብቃት እንዲሁም በፕሪምየርሊጉ ስምንተኛ ደረጃ ይዘው ለማጠናቀቅ ቢችሉም ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ከ”ቅዱሳኖቹ” ጋር ተለያይተዋል።

ከቡድኑ ኮከብ ተጫዋቾች ጋር መስማማት አለመቻላቸው እንዲሁም ግትር የሆነው የአጨዋወት መንገዳቸው ለስንብታቸው ምክንያት እንደነበር ይታወሳል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s