ሀሪ ኬን ዩናይትድን ከሚገጥመው የስፐርስ የቡድን ስብስብ ውጪ ሆነ

2.jpg

ዩናይትድ እና ቶተንሀም የሚያደርጉት የቅዳሜው የምሳ ሰአት ጨዋታ ላይ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው ሀሪ ኬን በጉዳት ከጨዋታው ውጪ መሆኑ ታውቋል፡፡

ሀሪ ኬን ስፐርሶች ሊቨርፑልን አስተናግደው በሰፊ ውጤት ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ መጠነኛ የቋንጃ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል፡፡

ጉዳቱ የነገው ወሳኝ ጨዋታ ሊያመልጠው እንደሚችል ሲነገር የቆየ ሲሆን ዛሬ የቡድኑ አሰልጣኝ ስለ ወቅታዊ የቡድናቸው የጤንነት ሁኔታ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተጫዋቹ ለጨዋታው የመድረስ እድል እንደሌለው አሳውቀዋል፡፡

 “ዶክተሮች እና የቡድኑ የህክምና አባላት በተጫዋቹ ሪስክ እንዳንወስድ ነግረውናል፡፡”በማለት ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ተጫዋቹ ከወሳኙ ፍልሚያ ውጪ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

ቡድኑ ያለ ሀሪ ኬን ወደ ሜዳ ከገባ ራቅ ያለ ጊዜ የተቆጠረ ሲሆን በኦልድትራፎርድ የሚያደርጉት ጨዋታም ለማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ከባድ ፈተና እንደሚሆን ተጠብቋል፡፡

ስፐርሶች የቻምፕየንስ ሊግ ጨዋታን ጨምሮ በቀጣዮቹ 12 ቀናት ውስጥ 4 ጨዋታዎች የሚያደርጉ በመሆኑ የተጫዋቹን መመለስ አጥብቀው ይፈልጉታል፡፡

 

2.jpg

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s