ቅዱስ ጊየርጊስ እና ወላይታ ድቻ በአሸናፊዎች አሸናፊ የፊታችን እሁድ ይጫወታሉ

picsart_09-24-04-52-012

ከዚህ ቀደም ከሊጉ መጀመር ቀደም ብሎ  ይደረግ የነበረው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ውድድር ለአመታት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዳግም ውድድሩ ለማካሄድ ቀን መቁረጡን ተከትሎ የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ እና የ2009 የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጥሎ ማለፍ አሸናፊ የነበረው ወላይታ ዲቻ የሚገናኙ ይሆናል፡፡

የፊታችን እሁድ በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስቴዲየም በሚደረገው በዚህ የአሸናፈ አሸናፊ ዋንጫ ውድድር ላይም ፈረሰኞቹ በጉዳት ምክንያት አስቻለው ታመነ ታደለ መንገሻ ሰላዲን ሰይድ እና ጋዲሴ መብራቴን የማያሰልፉ ሲሆን መጠነኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረው አብደልከሪም መሀመድ ከጉዳቱ ሙሉ በሙሉ ማገገሙን ተከትሎ በእሁዱ ጨዋታ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል፡፡

ስመ ጥሮቹን ወንደሰን አሸናፊ አላዛር ፋሲካ እና ፈቱዲን ጀማልን የሸኙት ወላይታ ዲቻዎች በእነርሱ ምትክ የቀድሞውን የንግድ ባንክ የግብ ዘብ ኢማኑኤል ፌቮ  እሸቱ መና እንዲሁም የአዋሳ ከተማውን አጥቂ ጃኮ አረፋትን  ያስፈረሙ ሲሆን የፊታችን እሁድም አዲሶቹን ፈራሚዎችን እንደሚያሰልፉ ይጠበቃል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s