ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያዊውን አጥቂ ሲዲ መሃመድ ኬታ አስፈረመ

Image may contain: 3 people, people smiling, people standing

በክረምቱ የዝውውር መስኮት በስፋት እየተሳተፉ የሚገኙት ፈረሰኞቹ የክለቡ 6ኛ ፈራሚያቸውን ዛሬ በኦፊሻል የፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ላይ በይፋ አስተዋውቀዋል፡፡

ላለፉት ሳምንታት በክለቡ የሙከራ ጊዜ ተሰጥቷቸው ከነበሩ ምዕራብ አፍሪካዊያን  የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ሲዲ መሃመድ ኬታ የሙከራ ጊዜውን በስኬት ማጠናቀቁን ተከትሎ ፈረሰኞቹን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዲ መሃመድ ኬታ ጨምሮ አሜ መሀመድ እና ኢብራሂም ፎፋናን በአጥቂ ስፍራ ላይ ያስረመ ሲሆን

ሲዲ መሃመድ ኬታ በፈረሰኞቹ ቤት ለቀጣዮቹ 2 አመታት ለመቆየት ፊርማውን ያኖረ ሲሆን በዘንድሮ የውድድር ዘመን በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ እና በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ጠንክረው ለመቅረብ ላሰቡት ቅዱስ ጊዮርጊሶችም  የማጥቃት ሀይላቸውን ያሰፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ማሊያዊው አጥቂ በባማኮ ክለብ ከ2010 እስከ 2013 ቆይታ ያደረገ ሲሆን ለተጨማሪ አራት አመታት ደግሞ በሌላኛው የማሊ ክለብ ሲኤስኬ ውስጥ በመጫወት ልምድ ማካበቱ የተነገረለት ሲሆን በቱኒዚያ ሊግም ዪኤስ ቤን ጉራደዳን ለወራት መጫወቱን የግል ማህደሩ ያመለክታል፡፡

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s