በአዲስ አበባ ስቴዲየም መቀመጫዎች ወንበር ከነበራቸው ስፍራዎች ውስጥ የካታንጋ ወንበር ሙሉ በሙሉ ተነስቷል

https://scontent.fjib1-2.fna.fbcdn.net/v/t1.0-9/22788958_1670827049655382_732447913295678333_n.jpg?oh=5c87beb81e58f7a19667d331c6f6287f&oe=5A689118

የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሊግ ሊጀመር የአንድ ሳምንት እድሜ ብቻ ቀርቶታል፡፡ 16 ክለቦች ተሳታፊ በሚሆኑበት በዚህ ውድድርም ከወዲሁ እንደስጋት  ከሚነሱ ነገሮች ግንባር ቀደሙ የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳይ ሲሆን ለዚህም እንደ አጋዥ ሆኖ ያገለግላል የተባለው የአዲስ አበባ ስቴዲየም የካታንጋ መቀመጫ ወንበር በሙሉ መነሳቱ እርግጥ ሆኗል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የፍጻሜ ውድድር ላይ በተጫወቱበት ወቅተ በሁለቱ ደጋፊዎች መካከል በተነሳው ጸብ ምክንያት በርካቶች ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታስ ሲሆን ከጉዳት ማድረሻ መሳሪያዎች መካከልም የስቴዲየም ወንበር ግንባር ቀደሙ እንደነበር  ታይቷል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ከወዲሁ ይህ ወንበር ካልተነቀለ ለወደፊቱ የስፖርታዊ ጨዋነት ሳንካ ይሆንብኛል በማለት ከሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ የካታንጋን ወንበሮች ያስነቀለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም የስቴዲየሙ የካታንጋ ወንበሮች ሙሉ በሙሉ ተነስቶ ልክ እንደ ቀድሞው ወንበር አልባ ሆኗል፡፡

የወንበሩን መነሳትም ተከትሎ ከዚህ ቀደም በወንበሩ መኖር ምክንያት በካታንጋ የሚገባውን የእግር ኳስ ተመልካች ቁጥር ይገደብ የነበረ ሲሆን  አሁን ግን የወንበሩን ከስፍራው መነሳት ተከትሎ ከከዚህ ቀደሙ ቁጥሩ ከፍ ያለ ታዳሚ ወደ ስቴዲየም እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s