ኢትዮጵያ ቡና ሰርቢያዊውን አሰልጣኝ ቀጠረ

Image result for kostadin papic

ባሳለፍነው አመት መጨረሻ ድራጋን ፓፓዲችን ዳግም የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው ክለቡ ዛሬ ደግሞ ፓፓዲችን ሸኝቶ ሌላኛውን ሰርቢያዊ አሰልጣኝ ኮስታዲን ፓፒችን መቅጠሩ እርግጥ ሆኗል፡፡

በ2008 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር መልካም የውድድር ዘመን ማሳለፍ የቻሉት አንጋፋው አሰልጣኝ ድራጋን ፓፓዲች ባሳለፍነው ወር በህመም ምክንያት ሆስፒታል ከገቡ በኋላ ዳግም ማገገም የተሳናቸው ሲሆን ሆስፒታሉም ሰርቢያዊው ካሁን በኋላ ጭንቀት እና ውጥረት ያለበት ስራ ላይ ከተሰማሩ ለህይወታቸው እንደሚያሰጋቸው መናገሩን ተከትሎም የኢትዮጵያ ቡና እና የድራጋን ፓፓዲች እህል ውሀ አብቅቷል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ሊግ የካበተ ልምድ ያላቸው ሰርቢያዊው አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ኮስታዲን ፓፒች ዛሬ ከስፖርት ዞን ጋር ባደረጉት ቆይታ  ሊጉ ሊጀመር የቀሩት ቀናት ጥቂት ቢሆኑም ባለኝ ልምድ ፈተናውን እወጣዋለው ያሉ ሲሆን በርካታ ደጋፊ ያለው ክለብ በማሰልጠኔ ለኔ መልካም ነው ከዚህ የተሻለ እንድጥር ያደርገኛል በማለት ፡፡ ቡናማዎቹን ለማሰልጠን መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል፡፡

በስመጥሮቹ ኦርላንዶ ፣ፓየሬትስ ኸርትስ ኦፍ ኦክ እና ካይዘርስ ቺፍስ የሰሩት ኮስታዲን ፓፒች የኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ጥቅምት 25 በእለተ ቅዳሜ በአዲስ አበባ ምሽት  11፡30 ከሲዳማ ቡና ጋር የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s