የካራባኦ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ድልድል ይፋ ሆነ

በቀድሞ ስሙ ካርሊንግ ካፕ ፣ ዎርዚንግተን ካፕ ፣ ሊግ ካፕ ፣ ካፒታል ዋን ካፕ እየተባለ ሲጠራ የነበረውና በዘንድሮው የውድድር ዘመን ካራባኦ ካፕ በሚል ስያሜ እየተካሄደ ያለው ውድድር ወደሩብ ፍፃሜው የደረሰ ሲሆን የአምናው ሻምፒዮን ማንችስተር ዩናይትድ ፣ የሊጉ ሻምፒዮን ቼልሲ እንዲሁም አርሰናልና ማንችስተር ሲቲን ያቀፈው የሩብ ፍፃሜ ድልድል ታውቋል፡፡

የአምናው ሻምፒዮን ማንችስተር ዩናይትድ ከስምንቱ ቀሪ ክለቦች ብቸኛው የሻምፒዮንሺፕ ክለብ የሆነውን ብሪስቶል ሲቲን ከሜዳው ውጪ የሚገጥም ሲሆን በኢዲ ንኬታህ ሁለት የመጨረሻ ግቦች በኖርዊች ከመሸነፍ የዳነው የአርሰን ዌንገሩ አርሰናል ቶተንሐምን በአስገራሚ ሁኔታ ጥሎ ከመጣው ዌስትሐም ጋር በለንደን ደርቢ ተደልድለዋል፡፡

የሻምፒዮንሺፑ መሪ የሆኑትን ዎልቭስን ተፈትኖ በፍፁም ቅጣት ምት ያሸነፈው ማንችስተር ሲቲ ከሌስተር ሲቲ ጋር መርሃ ግብሩን እንዲያደርግ የተደለደለ ሲሆን ኤቨርተንን ጥሎ የመጣው የአንቶኒዮ ኮንቴው ቼልሲ ከቦርንማውዝ ጋር የሩብ ፍፃሜ ጨዋታውን ያከናውናል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s