ፊፋ ለ 2018 የአለም ዋንጫ የሽልማት መጠን ማሳደጉን አሳወቀ

የአለም አቀፍ የእግርኳስ አስተዳዳሪ (ፊፋ) የፊታችን ሰኔ ወር ላይ ለሚጀመረው የ2018 የአለም ዋንጫ የሽልማት መጠን ማሳደጉን አሳውቋል።

32 ቡድኖች በሚሳተፉበት በአራት አመት አንድ ጊዜ የሚዘጋጀው የአለም ዋንጫ ሊጀመር ስምንት ወራት እድሜ ብቻ ቀርተውታል።

ራሺያ ዝግጅቷን ለማጠናቀቅ የመጨረሻ ምእራፍ ላይ ስትገኝ ተሳታፊ አገራትም በአብዛኛው እየተለዩ ይገኛሉ።

በአፍሪካ ዞን የሚደረጉ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታዎች እንዲሁም በጥሎማለፍ(ፕሌይ ኦፍ) ከሚደረጉ ጨዋታዎች ውጪ ወደ ራሺያ እነማን አገራት እንደሚያቀኑ ተለይተው ታውቋል።

ፊፋ በዚህ ውድድር ላይ ያዘጋጀው ሽልማት ከሌላው ጊዜ በተሻለ ማሳደጉን አሳውቋል።2014 ላይ ከነበረው የሽልማት መጠንም በ 12% ማሳደጉን ይፋ አድርጓል።

ብራዚል ላይ የተካሄደው የ 2014 የአለም ዋንጫ ላይ ፊፋ 358 ሚሊየን ዶላር ለሽልማት ሲያቀርብ በቀጣዩ የራሺያ የአለም ዋንጫ ግን 400 ሚሊየን ዶላር ለተሳታፊ አገራት የሚሸልም ይሆናል።

2014 ላይ አሸናፊ የነበረችው ጀርመን 35 ሚሊዮን ዶላር መሸለሟ የሚታወስ ሲሆን 2018 ላይ ግን አሸናፊው አገር 38 ሚሊዮን ዶላር ያገኛል።

ሁለተኛ እና ሶስተኛ የሚወጡት ደግሞ 28 ሚሊየን ዶላር እና 24 ሚሊየን ዶላር ሲሸለሙ ከምድቡ የሚሰናበት አገር ትንሹን 8 ሚሊየን ዶላር የሚሸለም ይሆናል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s