ማንችስተር ዩናይትድ ከ2007/08 የውድድር ዘመን ወዲህ አዲስ ያለመሸነፍ ታሪክ አስመዝገበ

ማን ዩናይትድ ከ2007/08 የውድድር ዘመን ወዲህ በተከታታይ በሜዳው ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ላይ መረቡን ያለማስደፈር አዲስ ክብረወሰን አስመዝግቧል።

የጆዜ ሞሪንሆ የአጨዋወት መንገድ ባለፉት ሳምንታት ትችት እየቀረበበት ሊገኝ ይችል ይሆናል። ነገር ግን ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ (ቅዳሜ) ከቀትር በኋላ በቶተንሃም ላይ የተቀዳጀው ድል የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት ተፎካካሪነት አቋም ላይ እንደሚገኝ ያመላከተ ሆኗል።

ሞሪንሆ ከሊቨርፑል ጋር በአቻ ውጤት የተለያዩበትና በኸደርስፊልድ ሽንፈት በደረሰባቸው ጨዋታ ጫና ውስጥ እንዲገቡ የሚያደረጋቸው አስተያየቶች ሲሰነዘሩባቸውም ነበር።

ይሁን እንጂ የአንቶኒዮ ማርሺያል ብቸኛ ግብ ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዘመን በኦልትራፎርድ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች መቶ በመቶ ስኬታማ እንዲሆን ማድረጉ በአሰልኙ ላይ የሚሰነዘሩ ሃሳቦች በሁለት ጎራ እንዲከፈሉም ምክኒያት ሆኗል።

ዩናይትድ በሜዳው ላይ ያደረጋቸውን አምስት ጨዋታዎች ማሸነፉ ብቻ ሳይሆን በእነዚህ ሁሉ ጨዋታዎች ላይ መረቡን አለማስደፈሩ ደግሞ በፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ የአጨዋወት መንገድ ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶች ውሃ የማያነሱ መሆናቸውን የሚያመላክት ይመስላል።

ዩናይትድ በሜዳው ባደረጋቸው ጨዋታዎች መሰል ውጤት ማስመዝገብ የቻለው በ2007/08 ከአስር ዓመታት በፊት ነበር። በዚያ የውድድር ዘመን ደግሞ ዩናይትድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ሆኗል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s