ስኬት / እንግሊዝ ከ 17 አመት በታች የአለም ዋንጫ አሸናፊ ሆነች

በህንድ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው ከ 17 አመት በታች የአለም ዋንጫ ውድድር እንግሊዝ በአስደናቂ ብቃት ስፔንን አሸናፋ የዋንጫ ባለቤት ሆነች።

እንግሊዞች ለወደፊት ወጣት ተስፈኞች እንዳሏት ባሳየችበት ውድድር ስፔንን 5-2 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆናለች።

በአስደናቂ ብቃት ከ 2-0 በመነሳት አምስት ጎሎችን ያስቆጠሩት ወጣቶቹ እንግሊዛዊያን ተጫዋቾች አከታትለው ያስቆጠሯቸው ጎሎች ለድል እንዲበቁ አድርጓቸዋል።

ለእንግሊዞች የማን ሲቲው አማካይ ፎደን  ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ትልቅ ሚና የተጫወተ ሲሆን ብሪዊስተር፣ጊብስ እና ጉሂ ቀሪዎቹን ጎሎች አስቆጥረዋል።

የሊቨርፑሉ አጥቂ ብሪውስተር ደግሞ በስምንት ጎሎች ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል።

ከጨዋታው በኋላ ስፔኖች በእንባ ታጥበው የታዩ ሲሆን በተቃራኒው እንግሊዞች በደስታ ሰክረዋል።

በርግጥም እንግሊዛዊያን አዳዲስ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣት ተጫዋቾች እንዳላቸው በሚገባ ማሳየት የቻሉ ቢሆንም በውጪ ተጫዋቾች የተጥለቀለቁት የፕሪምየርሊግ ክለቦች የእንግሊዛዊያን ወጣት ተጫዋቾቹን እድገት እንዳያቀጭጩት ተሰግቷል።

ለምሳሌ በዛሬው ጨዋታ ላይ ሁለት ጎል ያስቆጠረው ፎደን የማንቸስተር ሲቲ ወጣት ተጫዋች ሲሆን ሲቲዎች ለዋናው ቡድናቸው ከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ በማውጣት ተጫዋቾች እያዘዋወሩ መቀጠላቸው የወጣት ተጫዋቹ እድገት ላይ ተጽእኖ መፍጠሩ እንደማይቀር ይገመታል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s