በሰሜን አፍሪካዎቹ ሀያላን የተደረገው የካፍ ቻ/ሊግ የፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

ኢትዮጵያዊው በአምላክ ተሰማ የመሩት በአል አህሊ እና በዋይዳድ ካዛብላንካ መካከል የተደረገው የካፍ ቻምፕየንስ ሊግ የመጀመሪያ የፍጻሜ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ።

<!–more–>

በቦርግ ኤል አረብ ስታድየም የተደረገው የሁለቱ የሰሜን አፍሪካ ሀያል ቡድኖች ፍጥጫ ባለሜዳዎቹ ገና ጨዋታው ከመጀመሩ ቀዳሚ የሚያደርጋቸውን ጎል ማስቆጠር ችለዋል።

ሞአሜን ኤልዳዊ ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ በአስገራሚ ሁኔታ በግራ እግሩ የመታው ኳስ አል አህሊ መልካም አጀማመር እንዲያደርግ ቢረዳውም በመሪነት የቆዩት ለ 13 ደቂቃ ብቻ ነበር።

ዋይዳዶች በቀኝ መስመር ያሻገሩትን ኳስ ቤንቻርኪ ወሳኟን የአቻነቷን ጎል በጭንቅላቱ ማስቆጠር ችሏል።

ድንቅ እንቅስቃሴ በታየበት የመጀመሪያ ግማሽ ባለሜዳዎቹ በኳስ ቁጥጥር የተሻሉ ሆነው ቢታዩም ግልጽ የጎል እድሎችን ለመፍጠር ተቸግረው ታይተዋል።

በሁለተኛው ግማሽም እንዲሁ በሜዳቸው ሌላ ጎል ለማስቆጠር የተጉት አል አህሊዎች አስጨንቀው ተጫውተዋል።

ነገርግን በመጨረሻው የአደጋ ክልል በፈጠራ ረገድ ደከማ ስለነበሩ የዋይዳድን ተከላካዮችን ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

እንግዳዎቹ በጥልቀት አፈግፍገው በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት ሞክረዋል።በአንድ አጋጣሚም እስማኤል ኤል ሀዳድ ጎል ሊሆን የሚችል አጋጣሚ አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ጨዋታውም ሳይሸናነፉ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ለመልሱ ጨዋታ ዋይዳድ ካዛብላንካ የተሻለ እድል ይዘው መውጣት ቢችሉም በቀጣዩ ሳምንት በሜዳቸው የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።

ኢትዮጵያዊው ባምለክ ተሰማ ከሁለት የአል አህሊ የፍጹም ቅጣት ምት ጥያቄዎች ውጪ ጨዋታውን በሚገባ ተቆጣጥሮ ማጠናቀቅ ችሏል።

የመልሶ እይታ ምስሎች እንዳሳዩትም ከሆነ በአምላክ የወሰናቸው ውሳኔዎች ትክክለኛ መሆናቸው ሲሆን 81ኛው ደቂቃ ላይ ኤል ጋብር የፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ተጠልፊያለው ብሎ የወደቀበት ሂደት ሳይነካ ስለነበረ ቢጫ ካርድ መመልከት ይገባው ከነበረበት እና ካለፉበትአጋጣሚ ውጪ ጨዋታውን በሚገባ እንደመሩት መነገር ይቻላል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s