የርገን ክሎፕ ማን ሲቲዎች በጥር ወር የፕሪምየርሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናገሩ

​የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግን እየመሩ የሚገኙት ማንችስተር ሲቲዎች የፕሪምየርሊጉን ዋንጫ በጊዜ በጥር ወር ላይ አሸናፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ተናግረዋል።

በፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች በሰፊ ጎል እያሸነፉ መልካም አጀማመር ማድረግ ችለዋል።

በፕሪምየርሊጉም ይሁን በቻምፕየንስ ሊጉ ላይ ወጥ የሆነ አቋም በማሳየት የዘንድሮ ቡድናቸው ከሌላው አመታት አስፈሪ መሆኑን እያሳዩ ይገኛሉ።

የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕም ቡድኑ በዚህ አስደናቂ አቋሙ ከቀጠለ የፕሪምየርሊጉን ዋንጫ በጥር ወር ላይ ሊያሸንፍ እንደሚችል ተናግረዋል።

በቡድናቸው የመከላከል አጨዋወት እንቅስቃሴ እየተተቹ የሚገኙት የርገን ክሎፕ በማጥቃት እንቅስቃሴ የፕሪምየርሊጉን ዋንጫ ማንሳት እንደሚችሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ

“ፔፕ ጋርዲዮላን እና ማን ሲቲን ጠይቁ፣ምን ታስባላችሁ? በዚህ አጨዋወታቸው የፕሪምየርሊጉ ዋንጫ በጥር የሚያነሱ ይመስላሉ።

“በዚህ ወይም በዛ መንገድ ስለተጫወቱ አይደለም።ነገርግን ለቡድንህ የሚሆነውን ትክክለኛውን መንገድ በመጠቀምህ ነው።አካባቢህ ያሉ ሌሎች ቡድኖችንም ማክበር አለብህ።ምክንያቱም እነሱም ጥሩ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።” ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s