ሮሜሉ ሉካኩ እና የእድሜው ነገር

የማንችስተር ዩናይትዱ የአጥቂ መስመር ተሰላፊ ሮሜሉ ሉካኩ በአካሉ ግዙፍ እና ጠንካራ በመሆኑ እድሜው ከሰውነቱ ግዝፈት አንጻር የሚመጣጠን እንዳልሆነ የሚናገሩ አሉ።

ተጫዋቹ በተለይም በልጅነቱ እኩዮቹ ከሆኑት በሰውነቱ ግዙፍ፣ጠንካራ እና ጎሎችን ደጋግሞ ማስቆጠሩ እድሜውን ደብቋል የሚሉ ጥያቄዎች ይነሱ ነበር።

የድሮ ምስሎችም የሚያሳዩት ሉካኩ በቁመቱም ይሁን በግዝፈቱ የተለየ ተጫዋች እንደነበር ማስተዋል ይቻላል።

ሉካኩ በ 14 አመቱ

ይህንን በማስመልከት በ12 እና በ14 አመቱ ላይ የተጫዋቹ እናት እድሜውን ለማሳየት የትውልድ እለቱን የሚገልጸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት (Birth Cirteficate)ይዘው ለሌሎች ወጣት ተጫዋቾች ቤተሰቦች እንዲሁም ወደ ሜዳ በማቅናት ያሳዩ እንደነበር ወኪሉ ሚኖ ራዮላ ተናግሯል።

ሉካኩ ለቤልጄሙ አንደርሌክት የመጀመሪያውን የፕሮፌሽናል ጨዋታ ሲያደርግ እድሜው 16 የነበረ ሲሆን በወቅቱ ተማሪ ነበር።

በእንግሊዝ ቼልሲ፣ዌስትብሮም እና ኤቨርተን ቆይታ ካደረገ በኋላ ባሳለፍነው የዝውውር መስኮት በ 75 ሚሊየን ፓውንድ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ መቀላቀል የቻለ ሲሆን ወቅታዊ እድሜውም 24 ነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s