ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በፍራንክፈርት ማራቶን ድንቅ ውጤት አስመዘገቡ

በፍራንክፈርት ማራቶን ኢትዮጵያዊያኖቹ ሹራ ቶላ፣ከልክል ገዛኸን እና ጌቱ ፈለቀ በወንዶች ተከታትለው በመግባት ሲያሸንፉ ኬኒያዊቷ ቪቪያን ቺሩዮት በሴቶች አሸናፊ ሆናለች።

በጀርመን ፍራንክፈርት የተካሄደው የማራቶን ውድድር በወንዶች ኢትዮጵያዎቹ ከ አንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ተከታትለው በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆነዋል።

አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀው አትሌት ሹራ ቱራ ሲሆን የገባበትም ሰአት 2:05:50 ነው።ከልክል ገዛኸኝ በ 2:06:56 እንዲሁም ጌቱ ፈለቀ 2:07:46 በሆነ ሰአት ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ይዘው ተከታትለው ገብተዋል።

በወንዶቹ ኬኒያዎቹ በደረጃ ውስጥ መግባት ሳይችሉ ቢቀሩም ማርቲን ኮስጂ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል።

በወንዶቹ የተሸነፉት ኬኒያዊቹ በሴቶቹ የተካሱበትን ውጤት ሲያስመዘግቡ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በማስከተል ነበር።የኦሎምፒክ የ 5ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ቪቪያን ቺሮይት የርቀቱ አሸናፊ ሆናለች።

የ34 አመቷ ኬኒያዊቷ አትሌት ከትራክ ውድድሯን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረገችው ሙሉ የማራቶን ውድድሯን በድል ተወጥታለች።

አትሌቷ አሸናፊ ሆና የገባችበት ሰአት 2:23:35 ሲሆን ኢትዮጵያኖቹ የብሩጋል መለሰ እና መስከረም አሰፋ 2:24:30 እና 2:24:38 በመግባት ተከታትለው ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s