የዋትፎርዱ አጥቂ ትሮይ ዲኒ እና የአርሰናል ደጋፊዎች ሽኩቻ!

GettyImages-867457824

አርሰናል ወደ ቪካሬጅ ሮድ አቅንቶ በዋትፎርድ የ 2-1 ሽንፈት ካጋጠመው በኋላ አጥቂው ትሮይ ዲኒ በአርሰናል ላይ በሰጠው አስተያየት ተበሳጭተው የነበሩት የአርሰናል ደጋፊዎች ተጫዋቹን በሚፈልጉት ወቅት ትችታቸውን የሚቃርቡበት ምክንያት አግኝተዋል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት አርሰናሎች በቪካሬጅ ሮድ ዋትፎርድን ቀድመው መምራት ችለው ነገርግን በመጨረሻ ደቂቃ ላይ በተቆጠረባቸው ጎል እጃቸውን ሰጥተው በተመለሱበት ጨዋታ የዋትፎርዱ አጥቂ ትሮይ ዲኒ የአርሰናል ተጫዋቾች ላይ ጠንካራ ትችን አቅርቦ ነበር፡፡

“አርሰናሎች ፈሪ ናቸው፣ ወኔ የላቸውም፡፡” በሚል ጠንካራ ንግግር የተናገረው አጥቂው የሰጠው አስተያየት በመድፈኞቹ ደጋፊዎች ጭምር አልተወደደለትም ነበር፡፡

ትናንት ዋትፎርድ ከስቶክ ሲቲ ጋር ያደረገው ጨዋታ በመጨረሻዎቹ ደቂቃ ላይ ትሮይ ዲኒ ከ ዌልሱ ጆ አለን ጋር ለጠብ ተጋብዘዋል፡፡ብስጭት ውስጥ ገብቶ የነበረው ዲኒም የ ጆ አለን ፊት ጨምድዶ ተጫዋቹን አንጠልጥሎ በማንሳት ያልተገባ ባህሪ አሳይቷል፡፡

ድርጊቱ ቀይ ካርድ ያሰጠው የነበረ ቢሆንም የእለቱ ዳኛ ማይክል ኦሊቨር ሁለቱን ተጫዋቾች ቢጫ ካርድ አሳይተው አልፈዋቸዋል፡፡ነገርግን ግን የዋትፎርዱ አጥቂ ከአርሰናል ደጋፊዎች ትችት ሊያመልጥ አልቻለም፡፡

የመድፈኞቹ ደጋፊዎች ተጫዋቹ ከሳምንታት በፊት በክለባቸው ላይ በሰጠው አስተያየት በማስታወስ ተጫዋቹ ጆ አለን ላይ በሰራው ድርጊት ከ እግርኳስ ሊታገድ እንደሚገባው የእግርኳስ ማህበሩን እየጎተጎቱ ይገኛሉ፡፡

የቀድሞ ዳኛ የነበሩት ግርሀም ፖልም ተጫዋቹ ላይ ቅጣት ሊተላለፍ እንደሚችል ሀሳባቸውን ከሰጡት ውሰጥ ይጠቀሳሉ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s