የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋቾች ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሄደ

Image may contain: 2 people, people standing, suit and wedding

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና በናታኒየም አድቨርታየዚንግ ኤንድ ኤቨንት አማካኝነት የተሰናዳው የ2009 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ኳስ ኮከቦች ሽልማት ዛሬ ጠዋት በካፒታል ሆቴል ተደርጓል፡፡ በርካታ የእግር ኳስ አለም ሰዎች እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣናት እና የመገናኛ ብዙሀን በተገኙበት በዚህ ስነ ስርዓትም በ30 ዘርፎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኮከቦች ሽልማቱን አበርክቷል፡፡

ከጠዋቱ 4 ሰዓት በተጀመረው እና እስከ 7 ሰዓት ድረስ በዘለቀው በዚህ የሽልማት ስነ ስርዓት ላይም የከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እስከ 1ኛ ሊግ ድረስ ያሉ ኮከቦች ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በተለይም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂ እና ኮከብ ተጫዋች ምርጫ የበርካቶችን ቀልብ መሳብ የቻለ ነበር፡፡

በወንዶች እና በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ መልካም ብቃታቸውን ያሳዩ ተጫዋች ምርጫ በሴቶች ኮከብ ግብ ጠባቂ ምርጫ የተጀመረ ሲሆን የአዋሳ ከነማዋ ግብ ጠበቂ ትዕግስት አሰፋ በኮከብነት አብረዋት የቀረቡትን ሳሳሁልሽ ስዩም እና ታሪኳ በርገናን በመብለጥ የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ ጠበቂ ክብርን አግኝታለች፡፡

በወንድ የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ኮከብ ግብ ጠባቂዎች ሽልማት ስነ ስርዓት ደግሞ የመከላከያው አቤል ማሞ ሳይጠበቅ ውድድሩን በአሸናፊነት ተወጥቷል፡፡ በርካቶች ለቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዶንካራ ቅድመ ግምቱን በሰጡበት ውድድር የመከላከያው የግብ ዘብ  የተሻለ ድምጽ በማግኘት የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኗል፡፡

በሴቶች  የ2009 ኮከብ ተጫዋች ምርጫ  ሰናይት ቦጋለ ዙለይካ ጁሀድ እና ሎዛ አበራ የመጨረሻ 3 እጩዎች የነበሩ ሲሆን  በውድድሩምን ሎዛ አበራ እብላጫውን ድምጽ በማግኘት የመድረኩ ኮከብ ተጫዋች ተብላ ተሰይማለች፡፡ በዚህ ስነ ስርዓት ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግራ መስመር ተካላካይ ብርሀኑ ቦጋለ እህት ሰናይት ቦጋለ ከሽንፈቱ በኋላ በእንባ ታጥባ የታየች ታይታለች፡፡

በርካቶች በጉጉት በጠበቁት የ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ምርጫ የ2008  ኮከብ ተጫዋች  አስቻለው ታመነ ዘንድሮም በድጋሚ በ2009 ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡ በዚህ ዘርፍ ምንተ ስኖት አዳነ እና ሙሉአለም መስፍን ዴኮ እጩዎች ነበሩ፡፡

ሌላው በእለቱ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሴቶች እና ወንዶች ኮከብ ግብ አግቢዎች ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ጌታነህ ከበደ በ25 ግቦች እንዲሁም ሎዛ አበራ በ33 ግቦች ሊጎቻቸውን በከፍተኛ አግቢነት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የገንዘብ እና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በእለቱ ለዮርዳኖስ አባይ ልዩ ተሸላሚ በማድረግ ልዩ የዋንጫ ሽልማት ያበረከተለት ሲሆን ይህም በእለቱ በስፍራው የነበሩ እንግዶችን በሙሉ ያስደሰተ ነበር፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s