“ራሞን ሳንቼዝ ፒዥዋን”የሲቪያ የድል ቦታ! 

የስፔኑ ሲቪያ የሚጫወትበት ስታድየም ራሞን ሳንቼዝ ፒዥዋን ለሌሎች የላሊጋ ቡድኖች ሲኦል ለአንዳሉሺያኑ ተወካይ የድል ቦታ ሆኖ ቀጥሏል።


ሲቪያ የሜዳውን ያህል ስኬት ከሜዳው ውጪ ማስመዝገብ ቢችል ኖሮ የላሊጋው ዋንጫ አሸናፊ መሆኑ የሚያጠራጥር አልነበረም።

ቡድኑ ለመጨረሻ ጊዜ ሽንፈት የተጎነጨው በፈረንጆቹ ህዳር 6/2016 ሲሆን በወቅቱ አሸናፊ መሆን የቻለው ባርሴሎና ነበር።

ሲቪያ በሊዮ ሜሲ እና ልዊስ ስዋሬዝ ጎሎች ሽንፈት ከቀመሰ በኋላ ላለፉት አንድ አመት ምንም አይነት ሽንፈት በላሊጋው ሳያስተናግድ ጉዞውን ቀጥሏል።

በዚህ አንድ አመት ውስጥ ሁለቱን የማድሪድ ሀያላን ጨምሮ ሌሎች የላሊጋ ቡድኖችን በማሸነፍ ራሞን ሳንቼዝ ፒዥዋን የድል ስፍራ አድርጎታል።

ለሌሎች የላሊጋ ቡድኖች ሲኦል የሆነው ስታድየም የሲቪያ ያለመሸነፍ ግስጋሴን የቱ ቡድን ሊገታ ይችላል? የሚለው እስካሁን ምላሽ አላገኘም።

ቡድኑ በዘንድሮው የላሊጋ ውድድርም በሜዳው ያደረጋቸውን አምስት ጨዋታዎች በማሸነፍ የሜዳውን ድንቅ ጉዞ ቀጥሎበታል።

ባርሴሎና እየመራበት በሚገኘው የ2017/2018 የስፔን ላሊጋ ውድድር ሲቪያ በአምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s