በጀርመን ዲኤፍቢ ፖካል ካፕ የጥሎ ማለፍ ውድድር ከወዲሁ ጠንከር ያለ ድልድል ወጥቷል፡፡
ሁለቱ የቡንደስ ሊጋ ሀያላን ክለቦች የሆኑት ባየርሙኒክ እና ቦርሲያ ዶርትመንድ በጥሎ ማለፉ የሚገኛኙ ሲሆን ፡፡ በሌላ ጨዋታ ደግሞ ባየር ሊቨርኩሰን ከ ቦርሲያሞንቼግ ላርባህ እንዲሁም ሻልክ ከ ኮሎኝ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ከፍተኛ ግምትን አግኝቷል፡፡
ባሳለፍነው አመት በወርሀ ሚያዝያ የመድረኩ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ተፋለሚ የነበሩት ባየርሙኒክ እና ቦርሲያ ዶርትመንድ ከወዲሁ በአሁኑ ውድድር በጥሎ ማለፉ የተገናኙ ሲሆን የመከመሪ ጨዋታቸውንም በወርሀ ታህሳስ በሲግናል ኢዱና ፓርክ እንደሚያደርጉ የወጣው መርሀ ግብር ያሳያል፡፡
ባለፈው አመት ሁለቱ ክለቦች ባደረጉት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ቦርሲያ ዶርትሙንድ 3-2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍጻሜው ማለፉ የሚታወስ ነው፡፡
በያዝነው አመት 2ቱ ክለቦች በቡንደስ ሊጋው አንገት ለአንገት ተናንቀው በሊጉ የደረጃ በ3 ነጥቦች ልዩነት በሊጉ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን የያዙ ሲሆን በቡንደስ ሊጋውም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በወርሀ ጥቅምት መጨረሻ በሲግናል ኢዱና ፓርክ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
Advertisements