ከማንችስተር ሲቲ ውጪ ሁሉም ክለብ ችግር እንዳለበት የርገን ክሎፕ ገለፁ

የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ከመሪው ማንችስተር ሲቲ ውጪ የፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ተስፈኛ ክለቦች በሙሉ ችግር አለባቸው ብለው ያምናሉ። 

ቀዮቹ ምንም እንኳ አሁንም በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ከሚገኘው የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን በ12 ነጥቦች ዝቅ ብለው ቢቀመጡም፣ ቅደሜ ኸደርስፊልድን ታውንን 3ለ0 በሆነ ውጤት በመርታት በፕሪሚየር ሊጉ ያደረጉትን የሶስት ጨዋታዎች ያለድል የመጓዝ ጉዞ መግታት ችለዋል። 

የሲቲ አስደናቂ የሆነ ወቅታዊ የውጤት ጉዞም በቅርብ ከሚከተላቸውና በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ቶተንሃምን በኦልትረፎርድ 1ለ0 በመርታት ቀንደኛ ተቀናቃኙን እግር በእግር ከሚከተለው ማንችስተር ዩናይትድ በአምስት ነጥቦች ርቀው እንዲቀመጡ አስችሏቸዋል። 

ስፐርሶች በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ውድድሮች ተከታታይ ሁለት የጨዋታ ሽንፈት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ሁለቱም ሽንፈቶች የገጠሙት ደግሞ ሊቨርፑልን 4ለ1 በሆነ ውጤ ማሸነፍ እንዲችሉ ከፍተኛውን ሚና የተወጣውን ሃሪ ኬንን በጉዳት ምክኒያት ማጣታቸውን ተከትሎ ነው።  

በቶተንሃም ከባድ ሽንፈት የገጠማቸው ጀርመናዊው አሰልጣኝም ድንገተኛው የማውሪሲዮ ፖቸቲኖ የውጤት መውረድ ማንችስተር ሲቲን እግር በእግር መከተሉ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ የሚያመላክት ስለመሆኑ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
“እስካሁን ብዙም የሚባል ዕድል አልነበረንም። እውነተው ይህ ነው።” ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረው “ነገር ግን ዕድለኛ ካልሆኩ ብለህ አትጠይቅም። “ዕድል ወዴት ነው ያለኸው?” ተብሎ አይጠየቅም። ዕድል ወዳንት እስኪመጣ ድረስ መስራት ብቻ ይጠበቅብሃል።

“ፖቸቲኖ እኔ ያልኩትን ተነሳሳይ ነገር ስለመናገር አለመናገሩ አላውቅም። ነገር ግን ሃሪ ኬን ባልነበረባቸው ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት ገጥሞታል። ነገሮች እንዲህ ናቸው። ነገሮች ሊሆኑ የሚችሉትም እንዲህ ነው። 

“ከሁለት ሳምንት በፊት የሃሪ ኬን ቡድን አልነበረም። አሁን ደግሞ የሃሪ ኬን ቡድን ሆነ። በግልፅ እንደሚታየው ከሲቲ ውጪ ሁላችንም ችግሮች አሉብን።”

ዳንኤል ስተሪጅ ቶሚ ስሚዝ የፈፀመውን ስህተት ተጠቅሞ በኸደርስፊልድ ላይ ባስቆጠረው ግብ በአንፊልድ ተፈጥሮ የነበረውን ጭንቀት ከማርገቡ ቀድም ብሎ በመጀመሪያው አጋማሽ መሃመድ ሳላህ የፍፁም ቅጣት ምት አምክኗል። 

ክሎፕ ቡድናቸው በቶተንሃሙ ጨዋታ እና ከመጀመሪያው አጋማሽ ካሳየው ውጤት አልባ ብቃት ወጥቶ አሰድናቂ ምላሽ በመስጠቱ ደስተኛ ሆነዋል።

“መጥፎ ትችት በደረሰብህ የመጨረሻው ጨዋታህ በኋላ በእንደዚህ አይነት መንገድ ልትጓዝ በማትችልበት ጨዋታ “ይህን ያህል መጥፎ አይደለም።” የምትል መሆን ግልፅ ነው። ውጤቱ ግን መጥፎ ነበር። ጥሩ ምላሽ መስጠተችን ግን በጣም ወሳኝ ነገር ነው።” ሲሉ አሰልጣኙ አክለው ተናግረዋል።

“የእውነት ለመናገር በመጀመሪውያው አጋማሽ የጨወታው ድባብ ያን ያህልም ጨለምተኛ አልነበረም። በመሆኑም ከዚያ ወጥተን ያደረገንውን ነገር ያደረግነው የምርም ድንቅ ነበር።”

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s