ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሌላ ቅጣት ?

12.jpg

ፖርቹጋላዊው የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትናንትና ቡድኑ በጂሮና ሲሸነፍ የሰራው ጥፋት ምናልባትም ለሌላ ቅጣት ሊዳርገው እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡

ሪያል ማድሪድ በካታላኑ ጂሮና ጠንካራ ፈተና ገጥሞት እጁን በሰጠበት ጨዋታ ላይ የቡድኑ እንቅስቃሴ እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡፡ባለሜዳዎቹ ጨዋታውን መምራት የሚችሉበት አጋጣሚዎች መጠቀም ባለመቻላቸው እንጂ ቀድሞውኑ ሪያል ማድሪድ ጫና ውስጥ መግባት የሚችልበት አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡

ለሻምፕዮኖቹ ኢስኮ ግብ ጠባቂው የተፋውን ኳስ ተጠቅሞ የማድሪዱን ሀያል መሪ በማድረግ ለእረፍት ቢወጡም ባለሜዳዎቹ እጅግ የሚያስቆጩ ሁለት ኳሶች የግቡ አንግል ጎል እንዳይሆኑ አግዷቸዋል፡፡

ከእረፍት መልስ ይበልጥ ተጠናክረው የተመለሱት ጂሮናዎች ሁለት ጎል አስቆጥረው መረባቸውን በተጨማሪ ጎል ሳያስደፍሩ አሸንፈው ወጥተዋል፡፡

በጨዋታው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ቡድኑን ይዞ መውጣት ሳይችል የቀረ ሲሆን በጨዋታው ላይ አልፎ አልፎ ከርቀት ከሚመታቸው ሙከራዎች ውጪ ደካማ እንቅስቃሴ ማድረግ ችሏል፡፡

ውጥረት ውስጥ የገባው ሮናልዶ በአንድ አጋጣሚም የጂሮናውን  ተጫዋችን በእጁ እና በክንዱ ፊቱ ላይ መትቶት ለማለፍ ሲሞክር ተጫዋቹ ወድቆ ታይቷል፡፡ይህም ተጫዋቹን ለሌላ ቅጣት ሊዳርገው እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡

የማድሪዱ ኮከብ በአመቱ መጀመሪያ ላይ ዳኛን በመግፋቱ እና በሁለት ቢጫ ቅጣት በአጠቃላይ ለአምስት ጨዋታዎ ቅጣት ተጥሎበት እንደነበር ይታወሳል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s