“ሀሪ ኬን ወደ ሜዳ በመመለሱ የልብ ልብ ተሰምቶናል” ማውሪሲዮ ፖቼቲንሆ

Image result for Harry Kane 2017

ረብዕ ምሽት በሳምንቱ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ታላላቅ ከሆኑ ጨዋታዎች መካከል ከፍተኛ ግምትን በበርካቶች ማግኘት የቻለው የቶትንሀም ሆትስፐርስ እና የሪያል ማድሪድ ጨዋታ በዌምብሌይ ይካሄል፡፡ ከዚህ ጨዋታ ቀድም ብሎም 2 የቶትንሀም ጨዋታዎች በጉዳት ምክንያት ያመለጡት ሀሪኬን ወደ ሜዳ መመለስን ተከትሎ አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቾቲንሆ በራስ መተማመናቸው መመለሱን ገልጸዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም የቶትነሀሙ አለቃ ከጨዋታው አንድ ቀን ቀደም ብሎ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እርሱ ወደ ሜዳ በመመለሱ በጣም በራሳችን ተማምነናል፡፡ እርግጥ ነው ተጨማሪ አንድ ቀን ጨዋታውን ለማድረግ ስለሚቀረን 100 ፐርሰንት እርግጠኛ ሆኜ ስለ እርሱ መመለስ በድፍረት ለመናገር ባልችልም እርሱ ለእኛ ወሳኝ ተጫዋቻችን ነው ፡፡ በማለት የእንግሊዛዊው አጥቂ መመለስ የልብ ልብ እንደሰጣቸው አርጀንቲናዊው ተናግረዋል፡፡

ስፐርሶች ሊቨርፑልን 4-1 በረቱበት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ላይ ኮከብ ሆኖ ያመሸው እንግሊዛዊው ኢንተርናሽናል በብሽሽት ጉዳት ምክንያት በዚህ ጨዋታ ላይ ተቀይሮ ከወጣ በኋላ ቶትንሀም በካራባኦ ካፕ እና በፕሪሚየር ሊጉ ላይ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ያልተሰለፈ ሲሆን የሰሜን ለንደኑ ክለብምበ በሁለቱም ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ምድብ 8 የሚገኙት ቶትንሀም ሆትስፐርስ እና ሪያል ማድሪድ ከ15 ቀናቶች በፊት በሳንቲያጋ ቤርናቦ ባደረጉት የምድቡ 3ኛ ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ቶትንሀም ሆትስፐርስ ምድቡን በ7 ነጥብ እና በ5 ንጹህ ግቦች ምድቡን በ1ኛነት እየመራ ይገኛል፡፡

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s