ሎቭረን ቤተሰቦቹ ላይ ከደጋፊዎች የግድያ ዛቻ ቀርቦ እንደነበረ አሳወቀ

2

በዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ በሊቨርፑል ደካማ እንቅስቃሴ እያሳየው የሚገኘው ዲያን ሎቭረን ከደጋፊዎች ቤተሰቦቹ ላይ የሞት ዛቻ ቀርቦባቸው እንደነበር በይፋ አሳወቀ

ሎቭረን በተለይም ሊቨርፑል በቶተንሀም 4-1 በተሸነፉበት ጨዋታ ላይ ስህተት በመስራቱ ለከፋ ትችት ተጋልጦ የነበረ ሲሆን ቀደም ብሎ ለአቋሙ መውረድ ህመም እየተሰማው መጫወቱ ምክንያት ማድረጉ ይታወሳል፡፡

አሁን ግን ከሊቨርፑል ደጋፊዎች በማህበራዊ ሚድያ ላይ ቤተሰቡ ላይ የግድያ ዛቻ እንደሚያደርሱ መልእክት ደርሶት እንደነበር አሳውቋል፡፡

“ሰዎች ስለኔ ምንም ቢናገሩ ደንታ የለኝም ነገርግን ቤተሰቦቼን ሲያስፈራሩ በፍጹም ዝም ልል አልችልም፡፡”በማለት ከደጋፊዎች የሚያስጠላ መልእክት ደርሶት እንደነበር አሳውቋል፡፡

ወጥ አቋም ማሳት የተሳነው ሊቨርፑል በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ የቨርጂል ቫንዳይክን ዝውውር ማጠናቀቅ አለመቻሉ በተከላካይ ክፍሉ ላይ ዋጋ እየከፈለ እንዳለ የሚናገሩ በርክተዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ቡድኑ አሁንም ሌሎች የዋንጫ ተፎካካሪ ቡድኖችን በልጦ የፕሪምየርሊግ ዋንጫን የማንሳት እድሉ የጠበበ ሲሆን የቡድኑ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕም ማንቸስተር ሲቲዎች ቀደም ብለው የፕሪምየርሊግ ክብራቸውን እንደሚያውጁ እስከመናገር ደርሰዋል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s