ሞሪንሆ ከሜይዌዝር ጋር እንደሚመሳሰሉ ጋሪ ኔቭል ገለፀ

እንደቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ጋሪ ኔቪል ሃሳብ ከሆነ የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪንሆ ከዓለማችን ታላቁ ቡጢኛ ፍሎይድ ሜይዌዘር ጁኒየር ጋር የታክቲክ ተመሳስሎ አላቸው።

ሞሪንሆ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከሊቨርፑል ጋር 0ለ0 በተለያዩበት ጨዋታ ምንም አይነት የማሸነፍ እንቅስቃሴ አላደረጉም የሚል የሰላ ትችት የቀረበባቸው ቢሆንም፣ በፕሪሚየር ሊጉ ቅዳሜ ቶተንሃምን 1ለ0 በመርታት ቡድናቸውን በሁለትኛ ደረጃ እንዲቀጥል ማድረግ ችለዋል።

ከዩናይትድ ጋር ስምንት የሊግ ዋንጫዎችን ማሸነፍ የቻለው ኔቭል ፖርቱጋላዊው ታክቲካዊ አሰልጣኝ ምንም እንኳ ካደረጋቸው 50 ፍልሚያዎች ምንም አይነት ሽንፈት ባይደርስበትም ተፋላሚዎቹን አብዝቶ በመከላከል ተደጋጋሚ ትችቶች ከሚሰነዘሩበት ሜይዌዘር ጋር ሊነፃፀሩ እንደሚችሉ ተናግሯል።

“[የቶተንሃሙ አሰልጣኝ] ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ እና [የሊቨርፑሉ] የርገን ክሎፕ በማጥቃቱ ሚና ስመጥር አሰልጣኞች ናቸው።” ሲል ኔቭል ለስካይ ስፖርት ተናግሯል።

የቀድሞው የቀያይ ሰይጣኖቹ የመስመር ተከላካይ አክሎም “አንዳንድ ጊዜ ሞሪንሆ መከላከልን እንደመሳሪያ በመጠቀም ሰዎች የሚሰነዝሯቸውን ጡጫዎች ተጠቅመው ጉልብታቸውን እንዲያሟጥጡ በማድረግ በተወሰነ ማልኩም ሜይዌዘርን ይመስላል። 

“የርገን ክሎፕ ከተወሰኑ ሳምንታት በፊት በተደረገው በዚያ ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ መግባት እንደማይችል ተረድቶታል። ምክኒያቱም ‘እኔ ማደረግ በማልፈልገውን የሞሪንሆን ድንቅ ብቃት እንዳደርግ አስገድዶኛል።’ ሲል ነገሩን ተረድቷል። እንዲሁም ቶንሃምም ቅዳሜ ወደፊት የማምራቱ እምነት ላይ ችግር ነበረበት። 

“‘መልሶ ማጥቃትን እዚህ ላደርገው አልችልም። እራሱ ያደረገዋል።’ የሚል ሃሳብ  ወደአዕምሮው እንዲመጣና እንዲያስብም አድርጎታል። በራሳቸው ታክቲክ እንዲጠመዱ ማድረግን ማሰብ የሚችል ድንቅ አሰልጣኝ ማለትም እንዲህ ዓይነቱ ነው። ስለዚህ ያስመዘገባቸው ሪከርዶች የማይታመኑ መሆናቸው በተወሰነ መንገድ የተሻለ አክብሮት ሊቸረው የሚገባ ይመስለኛል።” በማለት ገልፅዋል።

ዩናይትድ ባደረጋቸው 10 የሊግ ጨዋታዎች 35 ግቦችን በማስቆጠር ዘጠኝ ጨዋታዎችን በመርታት የሊጉ የደረጃ አናት ላይ ተቀምጦ ከሚገኘው ከከተማ ተቀናቃኙ ማንችስተር ሲቲ በአምስት ነጥቦች ዝቅ ብሎ ተቀምጧል። 

ኔቭል የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ወቅታዊ ብቃት እና የዩናይትድ አዝናኝ ጨዋታዎችን የመጫወት ታሪክ ከሞሪንሆ አጨዋወት ጋር ግጭት እንደሚፈጥር ያምናል።

ይህን ሲገልፅም “ሁለቱ ችግሮቹ የከፍተኛ ስሜት ጉዳዮች ናቸው። የማንችስተር ዩናይትድ ታሪክና የፔፕ ጋርዲዮላ እግርኳስ።

“እነዚህ ደግሞ ባተወስነ መልኩ ችግር ይፈጥሩበታል። ነገር ግን እነዚያ የአትያየ ጉዳዮች ናቸው።” 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s