ዋልያው የ2018 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ለማጣት በእጅጉ ተቃርቧል

Image result for ethiopian national team

ግብፅ ከ2018 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ራሷን ማግለሏን ተከትሎ በሰሜን አፍሪኳዊቷ ሀገር ምትክ ሆነው እንዲገቡ ሩዋንዳ እና ኢትዮጵያ በጥሎ ማለፍ ጨዋታ እድል የተሰጣቸው ቢሆንም ዋልያዎቹ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ሊወስዳቸውን የሚችለውን ወርቃማ አጋጣሚ የመጠቀማቸው ነገር አጠያያቂ ሆኗል፡፡

ካፍ እድሉን ለሁለቱም ሀገራት እድሉን እንዲጠቀሙ ባሳወቀ ቀናት ልዩነት ውስጥ ከሩዋንዳ ብሄራዊ ቡድን ጋር ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ አሳውቀው የነበሩት ዋልያዎቹ የሊጉ መጀመር ቀናት መቃረብ እና የዝግጅት ጊዜ ማነስን ተከትሎ ለካፍ ጨዋታው ይራዘምልን ጥያቄ ቢያቀርቡም እስካሁን  ከካፍ በጎ ምላሽን አላገኙም፡፡

ጨዋታው እንዲካሄድ በጥቅምት 26 ቀነ ቀጠሮ ቢያዝለትም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እስካሁን ልምምድ ያልጀመረ ሲሆን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ላይ ተጫዋቾቹ እንዲሰባሰቡ ጥሪ ቢተላለፍላቸውም በስራ አስፈጻሚው ትህዛዝ መሰረት ተጫዋቾቹ ወደመጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

ይህ ብቻ ሳይሆን ለዚህ ጨዋታ ተብሎ ፕሪሚየር ሊጉ ለቀጣዮቹ 2 ሳምንታት እንደሚራዘም ቢሰማም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለ4ኛ ጊዜ ሊጉን ለማራዘም ፍቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በህዳር 26 የሚጀመር ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የፊታችን እሁድ ከሩዋንዳ አቻው ጋር ለቻን 2018 በጥሎ ማፍ ለማድረግ ይዞት የነበረውን  የመጀመሪያ ጨዋታ በዚህ ምክንያት የማድረጉ እድል በእጅጉ አጠራጣሪ አድርጎታል፡፡

የስራ ዘመኑን ለማጠናቀቅ ቀናት የቀሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሄራዊ ቡድኑ ለ3 ተከታታይ ጊዜያት  ከአፍሪካ ዋንጫ በመቀጠል ትልቅ ስም ባለው  የአፍሪካ መድረክ ውድድር ላይ እንዳይተፍ እንቅፋት የሆነ ሲሆን የፌዴሬሽኑ አመራሮችም ከብሄራዊ ቡድኑ ይልቅ  ለጥቅምት 30ው ምርጫ ሽርጉድ ማለታቸው ዋልያው ያገኘውን ወርቃማ እድል እንዳይጠቀም እነዳያደርገው ተሰግቷል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s