የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ቅድመ ቅኝት

የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ቅድመ ቅኝትበሻምፒዮንስ ሊጉ የምድብ ማጣሪያ አራተኛ ጨዋታዎች ዛሬ (ማክሰኞ) ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። እኛም ዛሬ ከሚደረጉት ከእነዚህ ጨዋታዎች አበይት የተባሉትን ጨዋታዎች ልናስቃኝዎ ወደድን።

<!–more–>
ሮማ ከ ቼልሲ 

ሮማና ቼልሲ በአሁኑ ጊዜ በሶስተኛ ደረጃ የሚገኘውን አትሌቲኮ ማድሪድን በልጠው በሻምፒዮንስ ሊጉ የምድብ ማጣሪያ የምድባቸውን የበላይ ሁለት ደረጃዎች ይዘው ጥሩ በሚባል መደላድል ላይ ይገኛሉ።
የሁለቱ ቡድኖች የመጨረሻ ጨዋታ ከሰምንታት በፊት በስታምፎርድ ብሪጅ ያደረጉት ጨዋታ ነበር። ጨዋታውም በ3ለ3 አቻ ውጤት ተጠናቋል።

የሁለቱ ክለቦች የእርስበእርስ ግንኙነት
ሁለቱ ክለቦች እርስበእርስ ተገናኝተው ባደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች አንድ አንድ ጨዋታ ሲሸናነፉ በአንዱ ጨዋታ ደግሞ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።
የቡድኖቹ ዜናዎች
ሮማ
አራቱ የተከላካይ ክፍል ተጫዋቾቹ ሪክ ካርስድሮፕ፣ ኑራ አብዱለሂ፣ ኮስታስ ማኖላስ እና ኤመርሰን በሙሉ በጉዳት ላይ ይገኛሉ።
ቼልሲ
ንጎሎ ካንቴ ወደልምምድ ቢመልስም በዚህ ጨዋታ ላይ ግን የመሰለፉ ነገር እርግጥ አይደለም። በጉዳት ላይ የሚገኘው ቪክቶር ሞሰስ አሁንም በጉዳት ይቆያል።
ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቤኔፊካ
በፕሪሚየር ሊጉ በአንቶኒ ማርሻል የጨዋታ መገባደጃ ሰዓት በተቆጠረች ግብ ቶተንሃምን ማሸነፍ የቻሉት ማንችስተር ዩናይትዶች ሙሉ ትኩረታቸው ወደሻምፒዮንስ ሊጉ ጨዋታ አዙረው እስካሁን በምድብ ማጣሪያው ባደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች ማግኘት የቻሉትን ድል አሁንም ለማስቀጠል እና እስከሁን በውድድሩ የተቆጠረባቸውን ብቸኛ ግብ ባለበት የማስቀጠል ውጥን ይዘው እንዱሁም በሁለተኛ ደረጃ የሚከተላቸውን ባሰልን በሶስት ነጥቦች በልጠው በምድቡ አናት ላይ በመቀመጥ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ቤኔፊካን በኦልትራፎርድ ይገጥማሉ።
ማንችስተር ዩናይትድ ይህን ጨዋታ አሸንፎ በስድስት ነጥቦች ከእሱ ዝቅ ብሎ በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሲኤስኬኤ ባስልን ማሸነፍ የማይችል ከሆነ ወደቀጣዩ የጥሎማለፍ ዙር አላፊ መሆኑን ያረጋግጣል።
የሁለቱ ክለቦች የእርስበእርስ ግንኙነት

ሁለቱ ክለቦች ለመጨረሻ ጊዜ ባደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ አራት ጨዋታዎችን በአሸናፊነት ሲያጠናቅቅ በሁለቱ አቻ ወጥቶ በአንዱ ደግሞ ሽንፈት ደርሶበታል።

የቡድን ዜናዎች
ማንችስተር ዩናይትድ አሁንም ማሩዋን ፌላኒ ፣ ማይክል ካሪክን፣ ፓል ፖግባን፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪችንና ማርኮስ ሮሆን በዚህ ጨዋታ ላይ የማያስለፍ ይሆናል።
በአንፃሩ የቤኔፊካው የቀኝ መስመር ተከላካይ አንድሬ አልሜዳ እና የመሃል ተከላካዩ ሉዊሳኦ በዚህ ጨዋታ ለይ ከቅጣት ምክኒያት የማይሰለፉ ተጫዋቾች ሲሆኑ ሌላው የቀኝ ተከላካይ ዳግላስ ኮስታ በዚህ ጨዋታ ላይ የማይኖር ተጫዋች ነው።


ኦሎምፒያኮስ ከ ባርሴሎና

ባደረጋቸው ሶሥት የምድብ ጨዋታዎች ሽንፈት የደረሰበትና በምድቡ የደረጃ ግርጌ ላይ የተቀመጠው የግሪኩ ክለብ ኦሎምፒያኮስ ወደቀጣዩ ዙር የማለፍ በጣም አነስተኛ ዕድል ይዞ በምድብ ማጣሪያ በቀዳሚነት የተቀመጠውንና በሁሉም ውድድሮች ላይ አስደናቂ ጉዞ እያደረገ የሚገኘውን ባርሴሎና በሜዳው ያስተናግዳል።
የሁለቱ ክለቦች የእርስበርስ ግንኙነት
በዚህ ወር መጀመሪያ በባርሴሎና የ3ለ1 ውጤት የተጠናቀቀው ጨዋታ የሁለቱ ክለቦች በታሪካቸው ያደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ነው።
የቡድን ዜናዎች
የባለሜዳው የግራ ክንፍ ተጫዋቹ ሴባ በጉዳት ምክኒያት በዚህ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ብቸኛ ተጫዋች ነው።
ተከላካዮቹ ቶማስ ቨርማለን እና አሌክስ ቪዳል፣ አማካኞቹ አንድሬስ ኢንየስታ፣ አርዳ ቱራንና ራፊንሃ እንዲሁም አጥቁው ኦስማኔ ዴምቤሌ በባርሴሎና በኩል በጉዳት ላይ የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው። ኻቪየር ማሼራኖ ከገጠመው ጉዳት በማገገሙ በቅጣት ላይ የሚገኘውን ጄራርድ ፒኬን በተከላካይነት ተክቶ ሊገባ ይችላል።
በሌላ በኩል ባሰል ከሲኤስኬኤ ሞስኮ፣ ፒኤስጂ ከአንደርሌክት፣ ሴልቲክ ከባየር ሙኒክ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከካራባግ እና ስፖርቲንግ ከጁቬንቱስ ምሽት 3፡45 ላይ የሚደረጉ ሌሎች የዛሬ ምሽት የጨዋታ መርሃግብሮች ናቸው።

Advertisements
Posted in Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s