ዲዲየር ዴሻምፕ ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ጋር እስከ 2020 ድረስ የሚያቆየውን ውል አራዝሟል

Image result for Didier Deschamps

የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን በማሰልጠን ውጤታማ ሊባሉ የሚችሉ ጊዜያትን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ፈረንሳዊው የቀድሞ የጁቬንቱስ አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሻምፕ ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ጋር እስከ 2020 ድረስ ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል፡፡

በ2012 የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን ማሰልጠን የጀመረው የቀድሞ የቼልሲ አማካይ ከፈረንሳይ ጋር በዩሮ 2016 የአውሮፓ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ የደረሰ ሲሆን በፍጻሜውም በፖርቱጋል 1-0 ተሸንፎ ዋንጫውን ማጣቱ ይታወሳል፡፡

የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ካደረገቻቸው 10 ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ተረታ ወደ አለም ዋንጫው ከምድቧ 1ኛ በመሆን እንድታለፍ ማድረግ ያስቻለው የ49 አመቱ ዲዲየር ዴሻምፕ ከወዲሁ ለ2018 የአለም ዋንጫ ሀገሩ ፈረንሳይን ብዙ ርቀት ይወስዳል ተብሎም እየተጠበቀም ይገኛል፡፡

የፈረንሳይ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ኖል ለ ግሬት “እርሱ ለእኔ ምርጡ አሰልጣኝ ነው ከማንም ጋር ላወዳደረው አልፈልግም ”  በማለት ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ  አሞካሽተዋል፡፡

የቀድሞ የቼልሲ እና ጁቬንቱስ የመሀል ሜዳ አማካይ ዲዲየር ዴሻምፕ በተጫዋችነት ዘመኑ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን በአምበልነት የመራ ሲሆን ሀገሩ ፈረንሳይም በእርሱ መሪነት የ1998 የአለም ዋንጫ እና የ2000 የአውሮፓ ዋንጫን ከፍ ማድረግ ችላለች፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s