ሰላዲን ሰይድ በአፍሪካ ሊግ የሚጫወቱ ኮከብ ተጫዋቾች እጩ ሆኗል

Image may contain: one or more people

ባሳለፍነው አመት ከክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ስኬታማ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ሰላዲን ሰይድ በአፍሪካ ሊግ የሚጫወቱ ኮከብ ተጫዋቾች እጩ ሆኗል፡፡ 30 በአፍሪካ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች በተካቱተበት በዚህ የኮከቦች ሽልማት ላይም የፈረሰኞቹ ፊት አውራሪ ሰላዲን ሰይድ ከ4 አመታት በኋላ ዳግም ለኮከብነት እጩ ሆኖ ቀርቧል፡፡

በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ለቅዱስ ጊዮርጊስ 7 ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ  ድንቅ ሊባል የሚችል  የውድድር አመት ከክለቡ ጋር ያሳለፈው የዋልያዎቹ የግብ ቀበኛ በ2013 በዚህ ሽልማት ላይ ከአዳነ ግርማ እና ጌታነህ ከበደ ጋር በመሆን በእጩ ውስጥ መካተት ችሎ የነበረ ሲሆን በወቅቱም በውድድሩ ሩቅ መጓዝ ሳይችል ቀርቶ ነበር፡፡

በ2 ዘርፎች ማለትም የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች እና በአፍሪካ ሊግ የሚጫወቱ ምርጥ ተጫዋቾች ሽልማት በሚል ካፍ ባሰናዳው እና የናየጄሪያው ስመ ጥር ኩባንያ አይቲኦ ስፖነሰር በሚያደርገው በዚህ የኮከቦች ምርጫ ላይ በሁለቱም ዘርፎች 30 ተጫዋቾች በድምሩ 60 የሚሆኑ እግር ኳሰኞች የታጩ ሲሆን አሸናፊዎቹም  ጃንዋሪ 4 በጋና አክራ በሚደረግ ዝግጅት ይፋ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

በዚህ ምርጫ ላይ የአፍሪካ ብሄራዊ ቡድን እና የክለብ አሰልጣኞች  ፣ ቴክኒካል ዳይሬክተሮች  ፣ የካፍ ቴክኒካል እና የልማት ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s