“ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በምናደርገው ጨዋታ መልሰን መፋለም ይኖርብናል።” – ቲብዋ ኮርትዋ

የቼልሲው ግብ ጠባቂ ቲቡዋ ኮርትዋ የቡድን አጋሮቹ እሁድ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በሚያደረጉት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ትናንት ምሽት በሻምፒዮንስ ሊጉ በሮማ የደረሰባቸውን የ3ለ0 ድል ለመቀልበስ መፋለም እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርቧል።

በማክሰኞ ምሽቱ ጨዋታ ዲያጎ ፔሮቲ የሮማን አሸናፊነት የምታረጋግጠውን የመጨረሻ ግብ በ63ኛው ደቂቃ ከማስቆጠሩ በፊት ኤል ሻራውይ በኮርትዋ ላይ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችሎ ነበር። 

ቼልሲ ከመስከረም ወር አንስቶ በሁሉም ውድድሮች ላይ መረቡን ሳያስደፍርው የወጣው በአንድ ጨዋታ ላይ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ የክለቡ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴም በሮማ የደረሰባሸውን ሽንፈት ተከትሎ ቡድናቸው ይበልጥ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባው ተናግረዋል።

ቼልሲ የጆዜ ሞሪንሆውን ቡድን የፊታችን እሁድ በስታምፎርድ ብሪጅ ያስተናግዳል። ኩርትዋም ቡድኑ መሻሻል እንዳለበት ሲገልፅ “ችግሩ ምን እንደነበር ለመናገር በጣም አስቸጋሪ ነው። በዚህ የውድድር ዘመን ሁሉም ጨዋታ አስቸጋሪ ነው። 

“ባለፈው የውድድር ዘመን አንዳንዴ በጨዋታዎች ላይ ምንም ሳላደርግ እወጣ ነበር። አንድ ኳስ ብቻ የማድንበትም ጊዜም ነበር። ለእኛ መጥፎ ገፅታ ያለው በመሆኑ በእሁድ ዕለቱ ጨዋታ ምላሽ መስጠት ይኖርብናል።

“ሚዛናችንን መልሰን ማግኘት ይኖርብናል። ግብ እንዳይቆጠርብን እና የለግብ የምንወጣበትን አስተሳሰብ መልሰን ማምጣት ይኖርብናል።

“ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በምናደርገው ጨዋታ መልሰን መፋለም ይኖርብናል።” በማለት ግብ ጠባቂው ተናግሯል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s