ዋልያው የቻን የማጣሪያ ጨዋታውን ከሩዋንዳ ጋር እንደሚያደርግ ፌዴሬሽኑ አረጋግጧል

Image result for ethiopia national team

በመጨረሻም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ የመጣለትን የቻን ተሳትፎ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ ጥያቄ ተቀብሏል፡፡ ፌዴሬሽኑ የተሰጠኝ ጊዜ አጭር ነው በማለት ለካፍ ጨዋታው የይራዘምልኝ ጥያቄን ቢያቀርብም ካፍ መልካም ምላሽ አለመስጠቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በታቀደለት ቀን እንዲደረግ ተወስኗል፡፡

ዛሬ ረፋድ በጉዳዩ ዙሪያ የመከሩት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ  እና  የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ብሄራዊ ቡድኑ የፊታችን እሁድ የሚደረገውን ጨዋታ እንዲያደርግ ከስምምነት የደረሱ ሲሆን ባሳለፍነው ሰኞ ጥሪ ተደርጎላቸው የነበሩ ተጫዋቾችም ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በካፒታል ሆቴል እንዲሰባሰቡ እና ከነገ ጀምሮም ልምምድ እንዲጀምሩ ከፌዴሬሽኑ ጥሪ እንደደረሰባቸው ተሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የሩዋንዳ ጨዋታ የፊታችን እሁድ ከሰዓት 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ላይ የሚካሄድ ሲሆን ይህንን ተከትሎም በእለቱ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ይደረግ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ከጨዋታው አንድ ቀን በፊት እንዲካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ መከላከያ እና ኢትዮጵያ ቡና ከ ሲዳማ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ በመጪው ሳምንት አጋማሽ እንዲደረግ መወሰኑ ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ለ2ኛው የቻን አፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ በ2005 ዓ.ም ተገናኝተው የነበረ ሲሆን በመጀመሪያው ጨዋታ ኢትዮጵያ በአስራት መገርሳ ብቸኛ ግብ 1-0 በሆነ ውጤት ስትረታ  የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ሩዋንዳ ኪጋሊ ላይ ዋልያውን በተመሳሳይ 1-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ  በተሰጠው የመለያ ምት ኢትዮጵያ 5-4 በሆነ ውጤት ማሸነፏ ይታወሳል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s